በኢትዮጵያ ከዓመታ በፊት የግሉ ዘርፍ፤ 12 ከመቶ ሰፋፊ እርሻ ያስተዳድር እንደነበረ ቢነገርም አሁን ግን ወደ 1 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጥናት አሳይቷል፡፡
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰት እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ያለ የሰላም እጦት ለዘርፉ መዳከም ከሚነሱት ቀዳሚ ችግሮች መካከል መሆናቸውን ሰምተናል፡፡
በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ የግል አልሚዎችም ለስራቸው መቀዛቀዝ የሚያነሱት ምክንያት ይህንኑ ነው፡፡
ከቅርብ አመታት ወዲህ እንደሀገር በተፈጠሩብን የሰላም መደፍረስ ችግሮች ምክንያት ዘርፉ የሚጠበቅበትን እየሰራ አይደለም የሚሉት የኢትዮጵያ ሰብል አምራቾች እና ላኪዎች ባለ ብዙ ዘርፍ ማህበር ፕሬዝደንት አቶ መልካሙ አብርሀም በተለያዩ አካባቢዎች ሰፋፊ እርሻዎች ላይ በፀጥታ ችግር የተነሳ ጉዳት መድረሱን ነግረውናል፡፡
በዚህ ምክንያትም በፍጥነት አገግሞ ወደ ስራ ያልተመለሱ እንዳሉ አቶ መልካሙ ይናገራሉ፡፡
Comments