ሐምሌ 11፣2015
ከአሜሪካ መከላከያ መስሪያ ቤት ፔንታገን በስህተት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የኤሌክትሮኒክስ መላ መልዕክቶችን ወደ ማሊ መላካቸው ተሰማ፡፡
በስህተት ከተላኩት የኢ-ሜይል መልዕክቶች ውስጥ ብርቱ ብርቱ ሚስጥሮችም የሚገኙባቸው እንዳሉ ቢቢሲ ፅፏል፡፡
የፔንታጎን ሹሞች ጉዳዩን በመላ እንይዘዋለን ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
ይሁንና ዋጋቸው ከፍ ያለ መረጃዎችን የያዙ መልዕክቶች እጅግ ሚስጥራዊ የሚል ፅሁፍ ያልሰፈረባቸው ናቸው ተብሏል፡፡
የማሊ ወታደራዊ መንግስት የሩሲያ ጥብቅ ወዳጅ መሆኑ ይነገራል፡፡
ከአሜሪካ የመከላከያ መስሪያ ቤት በስህተት ያፈተለኩትን ኢ-ሜይሎች ሌሎች ወገኖች ሊያገኟቸው መሞከራቸው እንደማይቀር መገመቱ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡
የኔነህ ከበደ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz
コメント