top of page

ሐምሌ 11፣2015 - በበጎ ስራዎቻቸው አርዓያ ናቸው የተባሉ 4 ወጣቶች ምስጋና ተሰጣቸው

በሽማግሌዎች ምርቃት ታጅበው ምስጋናው እና የእውቅና ሰርተፍኬት የተሰጣቸው ማስተር አብነት ከበደ፣ ወንድም ካሊድ፣ ሚኪያስ ለገሰ እና ዘካሪያስ ኪሮስ ናቸው፡፡


ለወጣቶቹ የዕውቅና ፕሮግራም የተሰናዳላቸው በጉለሌ ክፍለ ከተማ ደጋፊነት ኤሴቅ ሁነት አዘጋጅ ባሰናዳው ስነስርዓት ላይ ነው፡፡


እውቅናው ከተሰጣቸው መካከል አንዱ የሆነው ሚኪያስ ለገሰ የተቸገሩ ሰዎች እንዲረዱ እና ህክምና እንዲያገኙ የሚሰራው የሰሊሆም የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል መስራች ነው፡፡


ማስተር አብነት ከበደ በተለይ ደጋፊ፣ ጧሪ የሌላቸውን አረጋዊያንን ከበጎ ፍቃደኞች ገንዘብ በማሰባሰብ ቤት በማደስ፣ ልብስ፣ ምግብ በመስጠት ይታወቃል፡፡


ወንድም ካሊድ፣ የካሊድ ፋውነዴሽን መስራች ሲሆን እሱም በተመሳሳይ ኑሮ ፊቷን ያዞረችባቸውን ሶዎች ያግዛል፡፡


ዘካሪያስ ኪሮስ በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ እማማ ዝናሽ ከሚባሉ አረጋዊት ጋር በሚሰራቸው ቪዲዮዎች የሚታወቅ ሲሆን ደጋፊ ያጡ ሰዎችን በመርዳት ይታወቃል፡፡

በዛሬው የእውቅናና የምስጋና ፕሮግራም ላይ የጉላሌ ክፍለ ከተማ ሃላፊዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎችና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተገኝተዋል፡፡



ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

Comments


bottom of page