ሐምሌ 10፣ 2016
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአዲስ አበባ አጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ‘’የሽግግር መንግስት’’ አይኖርም ሲሉ የተናገሩት ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን እንደማይወክል ይታወቅልኝ አለ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፤ በወቅቱ በመደረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር ‘’የሽግግር መንግስት የሚል ሀሳብ ይነሳል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ከእንግዲህ የሽግግር መንግስት አይኖርም የሚኖረው በምርጫ የተመረጠ መንግስት ብቻ ነው’’ ማለታቸው ይታወሳል፡፡
ይህን ተከትሎም በርካቶች በምክር ሂደቱ የሽግግር መንግስት ይቋቋም የሚል አጀንዳ ቢቀርብ ‘’ተፈጻሚ አይሆንም ይህም መንግስት አጀንዳዎችን የመፈጸም ፍላጎት የለውም ኮሚሽኑም ውጤት ላያመጣ ይችላል’’ የሚል ሃሳብ ሲነሳ ቆይቷል፡፡
ለዚህም ምላሽ የሰጠው የምክክር ኮሚሽን እንዲታወቅልኝ የምፈልገው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ የተናገሩት የመንግስታቸውን እና ፓርቲቸውን ሀሳብ ነው ብሏል፡፡
ኮሚሽኑ ይህን የተናገረው በመጭው ሳምንት በጋምቤላ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፣ ሐረሪ እና በድሬዳዋ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት እንደሚጀምር በተናገረበት ወቅት ነው፡፡
ኮሚሽነር መላኩ ወለደ ማርያም ‘’ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በወቅቱ በመደረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር የመንግስታቸውን እና የፓርቲያቸውን አቋም ሊሆን ይችላል ይህ ማለት የእኛን አሰራር የኛን አካሄድ ይገዛል ማለት እንዳል ሆነ በግልጽ መታወቅ አለበት’’ ብለዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Website: https://www.shegerfm.com/
תגובות