top of page

ሐምሌ 10፣2016 - የአዲስ አበባ የቀድሞ ከንቲባና የማዕድን ሚኒስትር የነበሩት ታከለ ኡማ የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር አ.ማ ዋና ስራ እፈፃሚ ሆነው ተሾሙ

  • sheger1021fm
  • Jul 17, 2024
  • 1 min read

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቀድሞ ከንቲባ እንዲሁም የማዕድን ሚኒስትር የነበሩት ታከለ ኡማ የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር አ.ማ ዋና ስራ እፈፃሚ ሆነው ተሾሙ።


ሹመቱ የተሰጣቸው በጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ መሆኑን የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር በፌስቡክ ገፁ ተናግሯል።


ለአቶ ታከለ ሹመቱ የተሰጣቸውም ከትናንት ሐምሌ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑ ተነግሯል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔ አባል የነበረት አቶ ታከለ ከሚኒስትርነታቸው ከተነሱ በኋላ በትምህርት ላይ መቆየታቸው ይታወሳል።


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page