ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ያሉ ጥገኝነት ፈላጊዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቁጥራቸው እየጨመሩ ያሉት የሱዳን #ስደተኞች ሲሆኑ በሀገሪቱ ያሉት ስደተኞችም ከ1 ሚሊዮን መብለጡ ተሰምቷል፡፡
#ኢሰመኮ ከሰኔ 2015 ዓ.ም እስከ እስከ ሰኔ 2016 ዓ.ም ድረስ ያለውን ዓመታዊ ሮፖርት ከሳምንት በፊት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
ይህንን ተከትሎ በተለይ በመተማ አማራ ክልል እና በኩሩሙክ ጋምቤላ ክልል የሚገቡ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞች፣ ፍልሰተኞች ከቀን ቀደ ቀን ቁጥራቸው እየጨመረ መጥቷል፡፡
በዚህም በጋምቤላ ክልል 394,302 የሚሆኑ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች የሚኖሩ ሲሆን በሶማሌ ክልል ደግሞ 346,007 ጥገኝነት ጠያቂዎች አሉ ብሏል፡፡
በቤንሻንጉል ክልል 104,094 ስደተኞች ያሉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የተ.መ.ድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር በሚያዝያ ወር 2016 ዓ.ም ባወጣው መረጃ መሰረት 22,305ቱ በጦርነት ምክንያት ከሱዳን ሸሽተው የመጡ ናቸው ብሏል፡፡
በአዲስ አበባ 78,293 የተመዘገቡና በከተማ ለመኖር ፍቃድ ያገኙ ስደተኞች ይገኛሉ ይላል ሪፖርቱ፡፡
በአማራ ክልል የሚገኙ ስደተኞቸ ቁጥራቸው 43.178 ሲሆን 22,501 ኤትርራዊያን ስደተኞች በአለመዋጭ መጠለያ ጣቢያ እንደሚገኙ ሰምተናል፡፡
ማርታ በቀለ
Comentarios