top of page

ሐምሌ 10፣ 2016 - በአዲስ አበባ በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት፤ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ሊደረግ ነው

በአዲስ አበባ በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት፤ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ሊደረግ ነው፡፡


በከተማዋ ጠዋትና ማታ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲቀሳቀሱ ሊደረግ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ለሸገር ተናግሯል፡፡


ጎዶሎ ቁጥር እና ሙሉ ቁጥር የኮድ 2 ተሽከርካሪዎችን በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርግ የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቷል ያሉት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የትራፊክ ቁጥጥርና ሁነት አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አያሌው እቴሳ ናቸው፡፡


እቅዱ በ2 እና በ3 ወር ጊዜ ውስጥ፤ በከተማው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኮድ 2 ተሽከርካራች በፈረቃ አንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል ተብሏል፡፡


የኦሮሚያንና የፌዴራልን ታርጋ ሳይጨምር የአዲስ አበባ ታርጋ ብቻ ያላቸው ተሽከርካሪዎች ከ755,000 በላይ ናቸው ያሉት አቶ አያሌው ከእነዚህ ውስጥ የበዙት ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በመሆናቸው ነው ጠዋትና ማታ በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚደረገው ሲሉም ለሸገር ተናግረዋል፡፡


ወንድሙ ሀይሉ


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page