በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ታጣቂዎች በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ የመሳተፍ ፍላጎት ካላቸው ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲሳተፉ አደርጋለሁ ሲል የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ፡፡
ኮሚሽኑ ይህን የተናገረው በክልሎች አጀንዳ ለማሰባሰብ ዝግጅት ማጠናቀቁን ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡
በምክክር ሂደቱ በትጥቅ ትግል ላይ ያሉ አካላት የመሳተፍ ፍላጎት ካላቸው ደንነታቸው ተጠብቆ እንዲሳተፉ የማድረግ አቅሙ አለኝ ሲል ኮሚሽኑ አስረድቷል፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍር አርአያ ከታጣቂዎቹ ይሁንታ እስከተገኘ ድረስ የእነሱ ደህንነት ተጠብቆ በምክክር ሂደቱ እንዲሳተፉ የማድረግ ኮሚሽኑ አቅም አለው ብለዋል፡፡
ግን የእነሱ ይሁንታ ካልተገኘ መንግስትንም ሆነ የሚመለከተውን አካል ለመጠየቅ ኮሚሽኑ ይቸገራል ሲሉ ዋና ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መስፍን አርአያ በመጪው ሳምንት በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በድሬዳዋና በሐረሪ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ይጀመራል ብለዋል፡፡
በአፋር ደግሞ አሁን ላይ ከፍተኛ ሙቀት ስላለ በጥቅምት ወር አጀንዳ ማሰባሰብ እንደሚጀመር ኮሚሽነሩ አስረድተዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments