በሰሜን አፍሪካ የስፔን ይዞታ በሆነችው ካናሪ ደሴት የተቀሰቀሰ የሰደድ እሳት በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከቤት ንብረታቸው አፈናቀለ፡፡
የሰደድ እሳቱ የተነሳው ላ ፓልማ በተባለችዋ የደሴቲቱ ክፍል እንደሆነ ኢቭጊንግ ስታንዳርድ ፅፏል፡፡
የሰደድ እሳት የተቀሰቀሰባት ላ ፓልማ በቱሪስቶች መዳረሻነቷ የምትታወቅ ነች፡፡
ቱሪስቶችም ጉብኝታቸውን እያቋረጡ በመውጣት ላይ ናቸው ተብሏል፡፡
የሰደድ እሳቱ ከ10 በላይ ቤቶችን ማውደሙ ታውቋል፡፡
ቃጠሎ በፍጥነት ከስፍራ ወደ ስፍራ እየተዛመተ መምጣቱን ዘገባው አስታውሷል፡፡
የኔነህ ከበደ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33K
Comments