ሐምሌ 1፣ 2016 ‘’በከተማዋ ለአለመረጋጋት መንስኤ ናቸው’’ ያላቸውን ጉዳዮችን በጥናት መለየቱን የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተ/ት ጉባኤ ተናገረ
- sheger1021fm
- Jul 8, 2024
- 1 min read
የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ‘’ጽንፍ የረገጡ አስተምህሮቶችን ጭምሮ በከተማዋ ለአለመረጋጋት መንስኤ ናቸው’’ ያላቸውን በርካታ ጉዳዮችን በጥናት መለየቱን ተናገረ፡፡
የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጻሃፊ፤ መጋቢ ታምራት አበጋዝ ‘’ጽንፍ የረገጠ አስተምህሮ የሚሰብኩ ወይም ከኔ አስተምህሮ የተለየው ሁሉ ትክክል አይደለም የሚሉ የሃይማኖት አስተማሪዎች እየበረከቱ ነው ይህም ልክ አይደለም’’ ብለዋል፡፡
‘’አንዱ ስለሌላዉ ሃይማኖት እውቀት እና ግንዛቤ ሳይኖረው ሌላውን ሀይማኖት ማጣጣል መተቸት እና ማንቋሸሽ በአደባባይ እየተለመደ መጥቷል’’ ያሉት መጋቢ ታምራት ‘’ይህም ለአብሮነት አደጋ ነው’’ ሲሉ ተናረዋል፡፡
ለዚህም ሁሉም ስለራሱ ሃይማኖት ብቻ እንዲስተምር ጠይቀዋል፡፡
የሀማኖት ተቋማት ለህጻናት የሚሰጡት ግብረ ገብ ትምህርትም ከበፊቱ መቀነሱን ጉባኤው አካሄድኩት ያለው ጥናት አሳይቷል፡፡
ከዚህ በፊት በሰንበት ትምህርት ቤቶች እና በቁራን ትምህርት የህፃናትን ስነ ምግባር ለማነፁ በግብረገብ ላይ ጠንካራ ስራ ላይ ይሰራ ነበር ተብሏል፡፡
‘’የህጻናት ስብዕናን በመቅረጽ ድረሻቸዉ ከፍተኛ ነዉ’’ ያሉት የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሃፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ ‘’አሁን ግን ያ ወርዷል ይህንንም በጥናት ለይተናል’’ ብለዋል፡፡
በዚህም ምክንያት ‘’የስነምግባር ዝቅጥት እየገጠመን ፈተና ዉስጥ ገብተናል’’ የሚሉት መጋቢ ታምራት ‘’ስለዚህም ይህን የግብረ ገብ ትምህርት እንደገና መልሶ ማጠናከር ይገባል’’ ሲሉ መክረዋል፡፡
‘’በዚህም ሰዉ ሰውን፣ ታላቁን፣ ወላጁን፣ ሀገርን የሚያከብርበት ማድረግ ይገባል፤ ምክንያቱም እርስ በእርስ እንዳንከባበር የሚደርጉ በረካታ ችግሮች እየመጡ ነዉ’’ ሲሉ ተናረዋል፡፡
የአምልኮ ስፍራዎች እና የአደባባይ በአላትም ቢሆኑ የሚነሳባቸው ውዝግብ በአግባቡ ተይዞ መፍትሄ ካልተሰጣቸው የግጭት እና አለመግባባት ምክንያት ሊሆኑ እንደሚችሉ ጉባኤዉ አስረድቷል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ… https://tinyurl.com/mpb2wwp6
ያሬድ እንዳሻው
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Comments