የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ለ40/60 እና ለ20/80 ቤት ገንብቶ ለነዋሪዎቹ ለማድረስ ችግር ገጥሞኛል አለ፡፡
መንግስት አቅሙ ላላቸው መሬት እያቀረበ በማህበር ተደራጅተው ቤት እንዲገነቡ እያደረገ ነው ሲል ኮርፖሬሽኑ ተናግሯል፡፡
ይሁንና ይህ አቅሙ ላላቸው ብቻ እንጂ ሌሎችን ቆጣቢዎች አያካትትም ተብሏል፡፡
በአዲስ አበባ ለረጅም ዓመታት ቤት ለማግኘት የቆጠቡ ነዋሪዎች እኛ ቤት ሳናገኝ በኛ ገንዘብ መንግስት ለሌሎች ቤት ሰርቶ እየሰጠ ነው ይላሉ፡፡
ኮርፖሬሽኑ በበኩሉ በእነሱ ገንዘብ ሳይሆን በመንግስት አቅም የተገነቡ ቤቶችን ለልማት ተነሺዎች እንደተሰጠ ተናግሯል፡፡
በአዲስ አበባ ነዋሪ ከሚፈተንበት አንዱ ቤት ሲሆን ይህንን ችግር ለማሰስተካከል መንግስት የተቻለኝን ሁሉ እያደረግሁኝ ነው ይላል፡፡
ነዋሪዎች ደግሞ ቤት ለማግኘት ብለን ገንዘባችንን ለዓመታት ስንቆጥብ ብንቆይም መንግስት ቤቱን ሊያስረክበን አልቻልም የሚል ቅሬታን በተደጋጋሚ ሲያነሱ ይሰማሉ፡፡
ማርታ በቀለ
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Comments