top of page

ህዳር 9፣2017 - የአለም አራት ኮኮብ አየር መንገድ ደረጃ ዕውቅና እና ሽልማት ማግኘቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተናገረ

የአለም አራት ኮኮብ አየር መንገድ ደረጃ ዕውቅና እና ሽልማት ማግኘቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተናገረ፡፡


አየር መንገዱ በዓመታዊው APEX Passenger Choice Awards 2025 የአለም አራት ኮኮብ አየር መንገድ ደረጃ ዕውቅና እና ሽልማት አግኝቻለሁ ብሏል፡፡


ይህ የአለም አራት ኮኮብ አየር መንገድ ሽልማት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ከተረጋገጡ ጉዞዎች ከበረራ በኋላ ከመንገደኞች በተሰጡ ድምፆች መሰረት የተበረከተ መሆኑንም አስረድቷል፡፡

ሽልማቱ እና እውቅናው በአቪዬሽኑ ዘርፍ አለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ነው ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድ በማህበራዊ የትስስር ገጹ ላይ አስፍሯል፡፡


コメント


bottom of page