top of page

ህዳር 9፣2017 - ‘’ኤጀንሲዎች ከደመወዛችን እስከ 50 በመቶ ይቆርጡብናል’’ ተቀጣሪ ሰራተኞች

  • sheger1021fm
  • Nov 18, 2024
  • 1 min read

በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች ከመንግስት ፍቃድ ወስደው፣ ቢሮ ከፍተው ሠራተኛን ከሥራ የሚያገናኙ ኤጀንሲዎች በየ ቦታው ይታያሉ።


ኤጀንሲዎቹ #ሥራ_አጥነትን መቀነስ ላይ ያላቸው ድርሻ እንዳለ ሆኖ ህግን ባልተከተለ አሰራራቸው የሚወቀሱም አሉ።


በተለይ ደግሞ አንዳንድ ኤጀንሲዎች ተቀጣሪን ከቀጣሪው ሲያገናኙ፤ የተጋነነ የአገልግሎት ክፍያ(ኮሚሽን) ይቀበላሉ የሚል ቅሬታ ይቀርብባቸዋል።


ከተቀጣሪው ደመወዝ 50 ከመቶ በላይ የሚቀበሉ #ኤጀንሲዎች እንዳሉም ከተቀጣሪዎች ሰምተናል።


በዚህ ጉዳይ ላይ ቅሬታ አቅራቢ ተቀጣሪዎችን፣ ሥራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎችን እንዲሁም በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሀገር ውስጥ ሥራ ስምሪት ክፍልን ጠይቀናል።


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ...


ንጋት መኮንን

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page