top of page

ህዳር 8፣2016 ‘’በመንግስትና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መካከል የሚደረገው ድርድር ግልፅ ይደረግ’’

የተለያዩ ጥያቄዎች እንዳሏቸው የሚነገሩና ነፍጥ ያነሱ ቡድኖች በተለያዩ አካባቢዎች መኖራቸው ይታወቃል፡፡


ከመካከላቸው እራሱን ‘’የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት’’ ብሎ ከሚጠራው እና መንግስት ደግሞ ‘’ሸኔ’’ የሚል ስያሜ ከሰጠው ታጣቂ ቡድን ጋር መንግስት ለሁለተኛ ጊዜ ድርድር መቀመጡ እየተነገረ ነው፡፡


ከኢትዮጵያ ውጭ ለሁለተኛ ጊዜ ድርድር እየተደረገ መሆኑንም በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ከመወራቱ ባለፈ መንግስት እስከ ትናንት በስቲያ ድረስ በይፋ ያለው ነገር አልነበረም፡፡


የቀደመውና ውጤት ያልተገኘበት ድርድርም ዝርዝር ነገሩ ለህዝብ ይፋ ሳይደረግ ቀርቷል፡፡


አሁን የሚደረገው ንግግርና ድርድርም ለሀገር ሰላምን ለማምጣት እስከሆነ ድረስ ግልፅና ሂደቱም ለህዝብ በይፋ የሚነገር እንዲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠይቀዋል፡፡


ግልፅና አካታች ያልሆነ የጎራ ንግግር ዘላቂ ሰላም አያመጣም የሚል ስጋትም አላቸው፡፡



የኔነህ ሲሳይ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page