top of page

ህዳር 7፣2016 - የሀሳብ አመንጪ ተቋማት ለሀገር የሚያበረክቱትን ድርሻ ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል ተባለ

ይህ የተባለው ከሀሳብ አመንጪው(ቲንክ ታንከሮች) መካከል የሆነው የማህበራዊ ጥናት መድረክ ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ (Forum For Social Studies) 25ኛ የምስረታ በዓሉን ባከበረበት ወቅት ነው፡፡


በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች ማህበር ፣ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በኢትዮጵያ የሀሳብ አመጪ ተቋማት ለልማት ያላቸው ሚና ምንድነው የሚለውን አጫጭር ፅሁፎችን አቅርበዋል፡፡


የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር አምዲሳ ተሾመ በኢትዮጵያ ያሉ ሀሳብ አመንጪ ተቋማት ቁጥራቸው በእጅጉ አናሳ ነው ብለዋል፡፡ ይህንንም ማሻሻል እንደሚያሻ ተናግረዋል፡፡


ለማሳያም በአለም ላይ ከ6,500 በላይ የሀሳብ አመንጪ ተቋማት አሉ ያሉት ዶ/ር አምዲሳ ከዚህ ውስጥ የአፍሪካ ሀሳብ አመንጪ ተቋማት 200 ብቻ ሲሆኑ አሜሪካ ብቻዋን ከ1,800 በላይ ሀሳብ አመንጪ ወይም ቲንክ ታንክ በላይ አላት ብለዋል፡፡


ኢትዮጵያ ያላት ሀሳብ አመንጪ ተቋማት ከ10 እንደማይበልጡ ከመድረኩ ሰምተናል፡፡


በፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ የተሰሩ የጥናት ውጤቶችን ያብራሩ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ በኤስ ኤስ ፎረም ፎር ሶሻል እስተዲስ ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊና ምጣኔ ሀብታዊ የዳሰሱ የጥናት ውጤቶች ተከውነዋል ብለዋል፡፡ከተጠኑ ጥናቶች ውስጥ ትኩረት ያገኙና በመንግስት ፖሊሲ ጭምር ግብአት የሆኑት ብዙዎቹ ናቸው ብለዋል፡፡


በምጣኔ ሐብት ፣ በማህበራዊ ፣ በትምህርት የስራ መስኮች ለሀገር የሚበጁ ጥናቶች በኤፍ ኤስ ኤስ ተሰርቷል ብለዋል፡፡


በመድረኩ ላይ የተለያዩ የሀሳብ አመንጪ ተወካዮችና ምሁራን የታደሙ ሲሆን ኢትዮጵያ የሀሳብ አመንጪ ተቋማት ድርሻቸው ምንድነው፣ ምንስ ሰርተዋል፣ የሰሩትንስ መንግስት ይቀበላቸዋል ወይ የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡


ምላሽ የሰጡት ዶ/ር አምዲሳ ተሾመ ከዚህ በፊት የወጡ ጥናቶች ምን ያህል ተቀባይነት አላቸው የሚለውን ለማወቅ ያደረግነው ክትትል ከተሰሩ የጥናት ውጤቶች ውስጥ 36 በመቶዎቹ የሚሆኑት በተግባር ላይ መሆናቸውን አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ያሬድ እንዳሻውየሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqzComments


bottom of page