top of page

ህዳር 7፣2016 - በ14.5 ሚሊየን ዶላር የተገነባ የቧንቧ እና የመገጣጠሚያ ዕቃዎች ማምረቻ ፋብሪካ ነገ እንደሚመረቅ ተነገረ

  • sheger1021fm
  • Nov 17, 2023
  • 1 min read

በአዳማ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ውስጥ በ14.5 ሚሊየን ዶላር የተገነባ የቧንቧ እና የመገጣጠሚያ ዕቃዎች ማምረቻ ፋብሪካ በነገው ዕለት እንደሚመረቅ ተነገረ፡፡


በጋራ ኢንቨስትመንት የተቋቋመው ይህ ፋብሪካ አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የቧንቧ እና መገጣጠሚያ ዕቃዎችን ያመርታል ተብሏል።


ኢ ዜድ ኤም ትሬድ ኤንድ ኢንቨስትመንት (EZM Trading and Investment) የተሰኘ ኢትዮጵያዊ ኩባንያ ሪፎ (RiiFo) ከተባለ ድርጅት ጋር በፈጠሩት ጥምረት የተቋቋመ ፋብሪካ እንደሆነም ሠምተናል።


የፋብሪካው ምርቶች በተለያዩ ዘርፎች ያለውን የቧንቧ እና የቱቦ ዝርጋታ ስርዓት አቅርቦት እና ጥራት ችግር ይፈታሉ ተብሏል።

ምርቶቹን ከሌሎች ሀገራት ለማስገባት የሚወጣውን የውጪ ምንዛሪ እንደሚያስቀርም ተነግሯል።


የአዲሱ ፋብሪካ ምርቶች ገበያውን ሲቀላቀሉ ከ30 እስከ 40 በመቶ በሚደርስ የዋጋ ቅናሽ ተጠቃሚዎች መግዛት ይችላሉ ተብሏል።


ፋብሪካው በአዳማ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በ3000 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈ እንደሆነ ትናንት በሸራተን አዲስ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሲነገር ሠምተናል::


‘ዘመናዊ የፕላስቲክ ቧንቧና መገጣጠሚያ ማምረቻ ፋብሪካ’ የሚል ዕውቅና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እንደሰተጠውም ተጠቅሷል።


‘’ኢ ዜድ ኤም ትሬድ ኤንድ ኢንቨስትመንት’’ ከ ‘’ሪፎ’’ ጋር በመሆን አሁን ላይ ከ200 ለሚበልጡ ሰራተኞች ቋሚ፤ ለሌሎች 400 ቋሚ ያልሆነ የስራ ዕድል መፍጠሩ ተነግሯል።



ንጋቱ ረጋሣ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page