አክሱም ሰላም ከወረደ ሁለት ዓመታት ቢያስቆጥርም፤ የሚታሰበውን ያህል ቱሪስቶችን ሊጎበኟት አለመቻላቸው ተነገረ፡፡
የበርካታ ጥንታዊ ቅርስ መገኛ የሆነችው #አክሱም_ከተማ ከሰሜኑ ጦርነት ቁዘማ መላቀቋን ያነጋገርናቸው የከተማው ነዋሪዎች ያስረዳሉ፡፡
ባለፉት ዓመታት በሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረው #ጦርነት ምክንያት የቱሪዝም እንቅስቃሴ አክሱም ከተማ ውስጥ ተቋርጦ እንደነበር የነገሩን እነዚህ ነዋሪዎች አሁንም አክሱም ውስጥ ሰላም ቢሰፍንም በሚፈለገው ጎብኚ እየመጣ አለመሆኑን ይናገራሉ፡፡
አቶ ሰለሞን ተክላይ በሆቴል ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብት ሲሆኑ አክሱም ከተማ ሰላም ሆና ቱሪስቶችን እየጠበቀች ቢሆንም፤ እስካሁን በክልሉና በፌደራል መንግስት በኩል ተገቢው የማስተዋወቅ ስራ ባለመሰራቱ የቱሪስቶች ቁጥር ሊጨምር እንዳልቻለ ነግረውናል፡፡
በአስጎብኚነት ስራ የተሰማራው አቶ ሰለሞን ገብረፃድቅ በበኩላቸው አክሱም ከተማ እንግዶችን ለመቀበል ሙሉ ዝግጅቷን ካጠናቀቀች ቆየት ብሏል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ነገር ግን #ቱሪስቶች አክሱም ሰላም መሆኗን ስለማያውቁ እንቅስቃሴው ቀዝቃዛ መሆኑን ይናገራሉ፡፡
የቱሪዝም ሚኒስቴር የማስታወቂያ ዴስክ ኃላፊ አቶ ንጉሴ እሸቱ፤ በሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን የቱሪስት ስፍራዎች ለማስተዋወቅ እየሞከርን ነው ብለዋል፡፡
ነገር ግን የውጪ ሀገራት ኤምባሴዎች የጉዞ እቀባ መጣላቸው የውጪ ሀገራት ጎብኚዎች እንዳይገኙ ችግር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments