top of page

ህዳር 6፣ 2017 - በኢትዮጵያ ቁጥሩ እየበረከተ የመጣው የስኳር በሽታ ሰዎች ላይ የሚሰደርሰው ጫና እየበረታ ነው ተባለ

በኢትዮጵያ ቁጥሩ እየበረከተ ከመጣው ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ውስጥ በስኳር በሽታ ሰዎች ላይ የሚሰደርሰው ጫና እየበረታ ነው ተባለ፡፡


የዓይነት አንድ ወይም (Type One Diabetic) በብዛት የሚያዙት ታዳጊዎች በመሆናቸውም ወላጆች ላይ ያለውን ጫና ለመቀነስ እየሰራሁ ነው ሲል የኢትዮጵያ የስኳር ህመም ማህበር ተናግሯል፡፡


በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታሰበውን #የስኳር_ህመም_ቀን የተመለከተ አውደጥናት በአዲስ አበባ ተካሄዷል፡፡

የስኳር ህመም ስርጭት በዓለም አቀፍ ደረጃ ቁጥሩ እየሰፋ መምጣቱንና በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ ሀገራት ላይ በስኳር ህመም የሚያዙ ሰዎች ብዛት እየጨመረ መሆኑን የኢትዮጵያ ስኳር ህመም ማህበር ፕሬዝዳንትና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የውስጥ ደዌና የስኳር ሃኪም የሆኑት ጌታሁን ታረቀኝ(ዶ/ር) ነግረውናል፡፡


ህመሙ ከሚያደርሰው ጫና ውሰጥ የተወሰነውን ለመቀነስ ማህበሩ በተለይ በአይነት አንድ ስኳር ለተያዙ ታዳጊዎች የተለያየ ድጋፍ እያደረገ ነው ተብሏል፡፡


በተጨማሪም ድጋፉ ለሌሎችም እንዲዳረስ ማህበሩ በጋራ ከሚሰራባቸው ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ጋር በመሆን እያገዘ ነው ተብሏል፡፡


የስኳር ህመም ሲነሳ የመድሃኒት አቅርቦት ጉዳይ ብዙ ጊዜ ጥያቄ የሚነሳበት በመሆኑ የኢንሱሊንና ሌሎች መድሃኒቶችን በተመለከተ ሸገር ራዲዮ የጠየቃቸው የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን ንጉሴ አገልግሎቱ ለመጪዎቹ 9 ወራት ድረስ የሚሆን በቂ የመድሃኒት ክምችት እንዳለው ነግረውናል፡፡


ነገር ግን አለ የተባለው የስኳር መድሃኒት እጥረት በተረካቢ የጤና ተቋማት በኩል የሚፈጠር በመሆኑ ያንን ማስተካከል ላይ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ… https://tinyurl.com/33xu5y6v


ምህረት ስዩም


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


コメント


bottom of page