ከኢትዮጵያ የህዝብ ቁጥር 70 በመቶው በስራ እድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች መሆናቸውን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
ከመካከላቸው ግን አንድ አራተኛው የስራ እድል አላገኙም፡፡
የህዝብ ብዛት በየዓመቱ 2 ነጥብ 6 በመቶ እያደገ እንደመሆኑም በመጭው ጊዜ ከፍተኛ የወጣት ቁጥር ይኖራል ተብሎ ይገመታል፡፡
በመሆኑም የወጣቶቹን ቁጥር የሚመጥን የስራ እድል የሚፈጥር ኢኮኖሚ ከመገንባት ባሻገር መንግስት ወጣቶች ከሱስ የፀዱ ፣ አእምሯቸውም ያልታወከና የተማሩ እንዲሆኑ ካልሰራ ምርታማ ዜጋ ሊሆኑ አይችሉም ተብሏል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Commentaires