top of page

ህዳር 30፣2017 - በህገወጥ መንገድ በግል የመድኃኒት መሸጫዎች የሚሸጡ የተለያዩ መድሃኒቶች

ለመንግስት የህክምና ተቋማት የሚቀርቡ የተለያዩ መድሃኒቶች በህገወጥ መንገድ ወጥተው በግል የመድኃኒት መሸጫዎች የሚሸጡባቸው አጋጣሚዎች አሉ።


በዚህም ላይ ቅሬታ የሚያቀርቡ ብዙዎች ናቸው፡፡


በመንግስት የህክምና ተቋም ላይ በ200 እና በ300 ብር የሚገኙ እንደ ኢንሱሊን ያሉ #መድሃኒቶች በድብቅ ወጥተው በግል የመድኃኒት መደብሮች እስከ 1,200 ብር ድረስ ዋጋ እየተቆረጠላቸው እንደሚሸጡ ቅሬታ አቅራቢዎች ይናገራሉ።


ይህ የሚሆነው ሆን ተብሎ በሚፈጠር ሰው ሰራሽ ምክንያት እንጂ የመድኃኒቶች እጥረት በመኖሩ አይደለም ሲል የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ይናገራል።


ለመንግስት #የህክምና_ተቋማት የሚቀርቡ መድሃኒቶች በግል ተቋማትም እንዲገኙና እንደዚህ አይነት ችግር ዳግም እንዳይፈጠር ለግል የጤና ተቋማትና ማቅረብ እንደጀመረ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የግዥ አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ለሸገር ሬዲዮ ነግረዋል።


አገልግሎቱ በዋናነት መድሓኒትና የህክምና ግብአቶች የሚያቀርበው ለመንግስት ተቋማት ቢሆንም በጥቂት መጠን አሁንም የሚቀርብላቸው የግል ተቋማት እንዳሉ አቶ ሰለሞን ተናግረዋል።


በኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅርቦቱን ስራ ለማሻሻል ከውጪ ሀገራት ከሚገዛው በተጨማሪ ለሀገር ቤት አምራቾች ማበረታቻ በማድረግ ፍላጎቱን ለመሙላት የፖሊሲ ማሻሻያ ጭምር እንደተደረገለት ተነግሯል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ …


ምህረት ስዩም


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page