top of page

ህዳር 30፣2017 - ''ሳንቲምፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽንስ'' በ2016 በጀት ዓመት 44 ሚሊዮን የግብይት ልውውጦች ማካሄዱን ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Dec 9, 2024
  • 1 min read

የክፍያ ስርዓት ኦፕሬተር ሆኖ እየሰራ የሚገኘው ሳንቲምፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽንስ በ2016 በጀት ዓመት 44 ሚሊዮን የግብይት ልውውጦች ማካሄዱን ተናገረ፡፡


በዚህም 16 ቢሊዮን ብር በ #ሳንቲም_ፔይ በኩል ዝውውር መደረጉን ተናግሯል፡፡


ኩባንያው ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ከ15,000 በላይ ነጋዴዎችን ደንበኛ ማድረጉንም አስታውሶ በአሁኑ ሰዓትም የነጋዴ ደንበኞቹ ብዛት 20,840 መድረሱን አስረድቷል፡፡


ከሁለት ዓመት በፊት ፍቃድ ተሰጥቶት እየሰራ የሚገኘው ሳንቲምፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽንስ እስካሁን ከ26 ቢሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር በስርዓቱ አማካይነት መደረጉን አስረድቷል፡፡

ድርጅቱ ሰሞኑን ሁለተኛውን የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ያደረገ ሲሆነ 2016 በጀት ዓመት የስኬት እንደነበር ተናግሯል፡፡


ሳንቲምፔይ ባለፉት ሁለት ዓመታት የክፍያ ሥርዓቱን በማስተዋወቅ፣ ግንዛቤ በመፍጠር ስራዎች ላይ ማሳለፉን አስታውሶ በዚህም ከገንዘብ ዝውውር ላይ የአገልግሎት ክፍያ አለመውሰዱን ጠቅሷል፡፡


ይህም ሆኖ ግን በ2016 በጀት ዓመት በአጠቃላይ 152 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱንና ከግብር በፊት 86 ሚሊዮን ብር ማትረፉን በዓመታዊ ሪፖርቱ ላይ አስረድቷል፡፡


በአሁኑ ሰዓትም ከ12 ባንኮች ጋር ሥርዓቱን በማስተሳሰር እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡


ሳንቲም ፔይ ደንበኞች ለሚፈፅሙት ግብይት እና ለተጠቀሙት አገልግሎት በቀላሉ ክፍያ መፈፀም የሚያስችላቸው የክፍያ ሥርዓት ነው፡፡


ደንበኞች አገልግሎቱን ለማግኘትም ሳንቲምፔይ በየንግድ ማዕከላቱ ያከፋፈላቸውን ኪው አር ኮድ ስካን በማድረግ በቀላሉ ክፍያ መፈፀም የሚያስችል መሆኑ ተነግሯል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page