top of page

ህዳር 30፣ 2015- መቀመጫውን በትሪፖሊ ያደረገው የሊቢያ መንግስት ግሪክ ሉዓላዊነታችንን እየተዳፈረች ነው ሲል ቁጣውን አሰማ፡፡

  • sheger1021fm
  • Dec 9, 2022
  • 1 min read

ህዳር 30፣ 2015


መቀመጫውን በትሪፖሊ ያደረገው የሊቢያ መንግስት ግሪክ ሉዓላዊነታችንን እየተዳፈረች ነው ሲል ቁጣውን አሰማ፡፡


የትሪፖሊው መንግስት ባወጣው መግለጫ ግሪክ የባሕር ወሰናችንን እየተጋፋች ነው ማለቱን ዴይሊ ሳባሕ ፅፏል፡፡


እንደሚባለው ግሪክ ከክሬት ደሴት በስተደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ እያካሄደች ነው፡፡


ሊቢያ ደግሞ ይሄ በምስራቃዊ ሜዴትሬኒያን የሚገኝ የባህር ክፍል የገዛ የውሃ አካሌ ነው ትላለች፡፡


ግሪክ በበኩሏ ከ3 ዓመታት በፊት በቱርክ እና በሊቢያ መካከል የተደረሰውንየባህር ወሰን መከለያ ስምምነት እንደተቃወመችው ዘገባው አስታውሷል፡፡


የኔነህ ከበደ



ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page