የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢው ኤም ፔሳ ሳፋሪኮም (M-PESA) የደንበኞቼ ቁጥር 8.3 ሚሊዮን ደርሷል አለ፡፡
ይህም አምና በመስከርም ወር ከነበረው 1.2 ሚሊዮን ደንበኞች በ6 እጥፍ ብልጫ አለው ብሏል፡፡
በአጠቃላይ በኤም ፔሳ የተደረገው ግብይት ደግሞ 6.4 ቢሊዮን ብር መድረሱን ኩባንያው ለሸገር በላከው መግለጫ ጠቅሷል።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የግማሽ ዓመት አፈፃፀም በሁሉም አገልግሎቶቹ ስኬት ማስመዝገቡን ተናግሯል፡፡
ኩባንያው በኔትወርክ እና አገልግሎት ሽፋን ከአጠቃላይ ህዝቡ 46 በመቶ ደርሷል፣ ይህም ከ12 ወራት በፊት ከነበረውጋር ሲነጻጸር 30 በመቶ እድገት አሳይቷል ብሏል።
በመላ ሀገሪቱ ከ3,000 በላይ የኔትወርክ ማማዎችን መገንባቱን የጠቀሰው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት የሞባይል አገልግሎት ንቁ ደንበኞቹ ከ6.1 ሚሊዮን በላይ መድረሳቸውን አስረድቷል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
Comments