ህዳር 3፣ 2017 - ''የተሽከርካሪዎች የጭነት ክብደት መጠን ለመወሰንና ለመቆጣጠር ተብሎ የወጣው ደንብ የኑሮ ውድነቱን ያባብሰዋለል'' የተሽከርካሪ ባለንብረቶች
- sheger1021fm
- Nov 12, 2024
- 1 min read
የተሽከርካሪዎች የጭነት ክብደት መጠን ለመወሰንና ለመቆጣጠር ተብሎ የወጣው ደንብ የኑሮ ውድነቱን ያባብሰዋለል በሚል የተሽከርካሪ ባለንብረቶች ተቃውሞ አቀረቡ።
የተሽከርካሪዎችን የጭነት ክብደት መጠን ለመወሰን እና ለመቆጣጠር የወጣው ደንብ አንድ ተሽከርካሪ ከ350 ኩንታል ወይም ከ35 ቶን በላይ መጫንን የሚከለክል ነው።
በዚህ ጉዳይ ላይ ያነጋገርናቸው የተሽከርካሪ ባለንብረቶችም የተሽከርካሪ የጭነት ክብደት መጠን ገደብ መጣሉ ለተሽከርካሪዎች እና ለመንገዶች ደህንነት ታስቦ ቢሆንም የጭነት መጠኑ ላይ የተወሰነ መሻሻል መደረግ አለበት ብለዋል።
ይህ ካልሆነ ግን የኑሮ ውድነቱን ያባብሰዋል ሲሉ ነግረውናል።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር አለሙ ስሜ በተሽከርካሪዎች ላይ የወጣው የክብደት መጠን ወሰን ለተሽከርካሪዎች እና ለመንገዶች ደህንነት ታስቦ ነው፤ የልኬት መጠኑም የተጋነነ አይደለም ብለዋል።
ፍቅሩ አምባቸው
Comments