በየቦታው በሚጠየቅ የተሽከርካሪ የኮቴ ክፍያ ምክንያት የተሽከርካሪ ባለንብረቶች መማረራቸውን ተናገሩ፡፡
በየመንገዱ #ኬላ እየዘረጉ ገንዘብ የሚጠይቁ ከጊዜ ወደ ጊዜም እየጨመሩ መሆናቸውም ተናግረዋል።
የፀጥታ ችግር ያለባቸው አካባቢዎች ላይ ችግሩ ይሰፋልም ሲሉ ነግረውናል።
በየጊዜው የሚጠየቀው የኮቴ ክፍያ እና በሽከርካሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው እንግልት፣ ምርቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዳይገቡ መስተጓጎል ከመፍጠር፣ በየጊዜው የሚጠየቀው ክፍያ ማሻቀብም ምርቶች ላይ #ዋጋ እንዲጨምር ያደርጋል ብለዋል።
የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በበኩሉ #የኮቴ_ክፍያ ህገ-ወጥ ስለሆነ እንዲቀርም ከክልሎች ጋር እየተናገርን ነው ብሏል፡፡
ፍቅሩ አምባቸው
Commentaires