top of page

ህዳር 3፣2016 - ኢትስዊች ‘’የብሔራዊ ክፍያ ጌትዌይ’’ ሙከራን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን ተናገረ

ኢትስዊች፤ ከሁሉም ባንኮች የክፍያ ስርዓት አፕሬተሮቸ በበይነ መረብ ለተደረገ ግብይት ክፍያ መፈፀም የሚያስችለው ‘’የብሔራዊ ክፍያ ጌትዌይ’’ ሙከራን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን ተናገረ።


የብሔራዊ ክፍያ ጌትዌይ የሙከራ ሂደቱ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ካገኝ ከሐምሌ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ሲከናወን መቆየቱን ተነግሯል፡፡


የብሔራዊ ክፍያ ጌትዌይ ላለፉት 3 ወራት በተወሰኑ የፋይናንስ ተቋማት እና የንግድ ተቋማት በኩል የተግባር ሙከራ ሲፈተሽ የቆየ ሲሆን፤ ሙከራው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆ በቅረቡ ሙሉ በሙሉ ለመጀመር አስፈላጊ ዝግጅቶች ተጠናቋል ተብሏል።


የብሔራዊ ክፍያ ጌትዌይ የሙከራ ሂደቱ በመሳካቱ የሁሉም ባንኮች፣ የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋማት፣ የክፍያ ሥርዓት ኦፕሬተሮች እና የክፍያ መፈፀሚያ ሰነድ አውጪዎች እንዲቀላለቁ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡


በክፍያ ጌትዌይ የደንበኞችን የባንክ ሒሳብ በማገናኘት ደንበኞች ለሶስተኛ ወገን ገንዘብ በተለያዩ የመክፈያ ዘዴዎች ማለትም በክሬዲት ካርድ፣ በዴቢት ካርድ፣ በሞባይል ገንዘብ መክፈል ያስችላቸዋል ተብሏል።


ደንበኞች በበይነ መረብ አማካይነት ለሚፈፅሙት ግዢ ክፍያውን ካሉበት ሆነው ከሁሉም ባንኮች እንዲሁም ከከፍያ ኦፕሬተሮች በኢትስዊች የክፍያ ጌትዌይ አማካይነት መፈፀም እንደሚችሉ ተነግሯል።


የኢትስዊች ዋና ሥራ አስፈጻሚ የአቶ ይለበስ አዲስ ብሔራዊ የክፍያ ጌትዌይ ቀልጣፋ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ምቹ ግብይት ማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የዲጂታል መድረክ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የብሔራዊ ክፍያ ጌትዌይ የፋይናንስ ተቋማት እና የዲጂታል ፋይናንሺያል አገልግሎት አቅራቢዎች ፈጣን፣አስተማማኝ እና ምቹ የኢ-ኮሜርስ ክፍያዎችን በተለያዩ የክፍያ መንገዶች እንዲፈጽሙ የሚያስችል ሲሆን ለበርካታ ፋይናንስ ተቋማት የክፍያ ጌትዌይ መሆኑ ተነግሯል፡፡


የብሔራዊ ክፍያ ጌትዌይ የፋይናንስ ተቋማትን እና የንግድ ተቋማት የኢ-ኮሜርስ አገልግሎትን እንዲቀላቀሉ ያስችላል ተብሎለታል።


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ ብሔራዊ ባንክም ፕሮጀክቱን ሲያስጀምር ይዞት የተነሳው ዓላማ ለሀገሪቱ ወጥ የሆነና ደረጃውን የጠበቀ የክፍያ ሥርዓት መፍጠር ነው ብለዋል።


ኢትስዊች፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ጨምሮ በሁሉም የግል እና የመንግስት ባንኮች፣ አነስተኛ የፋይናስ ተቋማት፣ የክፍያ ስርዓት ኦፕሬተሮችና የክፍያ መፈፀሚያ ሰነድ አውጪ ድርጅቶች ባለቤትነት የተቋቋመ ኩባንያ ነው፡፡


ኩባንያው በፋይናንስ ተቋማት መካከል ተናባቢነት እንዲኖር የክፍያ ስርዓትን ለማቅረብ፣ የብሔራዊ ክፍያ ጌትዌይ አገልግሎትን ለመስጠት እና ለፋይናንስ ተቋማት የጋራ መሰረተ ልማት ለማቅረብ እየሰራ ይገኛል ተብሏል፡፡

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page