top of page

ህዳር 28፣2017 - ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ በ2016 በጀት ዓመት 1.24 ቢሊዮን ብር የአረቦን ገቢ  ማግኘቱን ተናገረ።

  • sheger1021fm
  • Dec 9, 2024
  • 1 min read

ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ በ2016 በጀት ዓመት 1.24 ቢሊዮን ብር የአረቦን ገቢ  ማግኘቱን ተናገረ።


ከግብር በፊት  462.1 ሚሊዮን ብር ማትረፉን አስረድቷል።


ኩባንያው በ2016 በጀት አመት ያገኘው የአረቦን ገቢ  ካለፈው በጀት ዓመት ከተገኘው 1.09 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር  የ13.3 በመቶ ዕድገት አለው ብሏል።


ኩባንያው ይህን የተናገረው  በዛሬው እለት ባካሄደው አመታዊ የባለ አክሲዮኖች ጉባኤ ላይ ነው።

ናይል ኢንሹራንስ 1.24 ቢሊዮን ብር የአረቦን ገቢ ያገኘው "በገበያው ውስጥ በተስተዋለው ዋጋን መሠረት ያደረገ እልህ አስጨራሽ ውድድር ውስጥ" ነው ሲሉ የኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድ  ሰብሳቢ አቶ  መሐሪ አለማየሁ ተናግረዋል።


የኩባንያው በበጀት ዓመቱ ያገኘው የተጣራ አረቦን ገቢ በ2015 በጀት ዓመት ከነበረው  723.3 ሚሊዮን ብር  ጋር ሲነጻጸር በ32.7 በመቶ ጭማሪ በማሳየት  959.9 ሚሊዮን  ብር ሆኗል ተብሏል፡፡



ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ በበጀት ዓመቱ በሁሉም ዘርፎች በድምሩ  ያልተጣራ 464.4 ሚሊዮን የካሳ ክፍያ መፈፀሙን ይህም ከለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር  የ22.5 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡


ለጠለፋ ዋስትና ሰጪዎች የሚከፈለው  41.2 ሚሊዮን  ብር ከተቀነሰ በኋላ የኩባንያው የተጣራ የካሳ ክፍያ 423.2 ሚሊዮን ብር መሆኑ በሪፖርቱ ተጠቅሷል።


ናይል ኢንሹራንስ በበጀት ዓመቱ የኢንቨስትመንት እና ሌሎች ገቢዎችን ሳይጨምር 468.8 ሚሊዮን  ብር ከመድን ውል ሥራ ትርፍ አግኝቻለሁ ብሏል፡፡


ኩባንያው ከኢንቨስትመንት ያገኘው ገቢ በ12 በመቶ ዕድገት በማሳየት 249.3 ሚሊዮን ብር መሆኑን  ተናግሯል።


ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ በ2016 በጀት ዓመት ከግብር በፊት  462.1 ሚሊዮን ብር ማትረፉን አስረድቷል። ትርፉ በቀዳሚው በጀት ዓመት ከተገኘው የ40.1 በመቶ ዕድገት አለው ሲል አስረድቷል፡፡


ኩባንያው በሪፖርት ዓመቱ ለ አንድ ሺህ ብር የአክሲዮን ዋጋ የተደለደለው የአክሲዮን ትርፍ 419  ብር ሲሆን በቀዳሚው ዓመት ከተመዘገበው  396 ብር ጋር ሲነጻጸር የ5.8 በመቶ ብልጫ አለው ብሏል፡፡


በዚህም መሰረት ኩባንያው ያገኘው የተጣራ  352.8 ሚሊዮን ብር ትርፍ  ለባለአክሲዮኞች ባላቸው የአክሲዮን መጠን እንዲከፈል ተወስኗል።


የኩባንያው ጠቅላላ ሀብት 4.2 ቢሊዮን ብር ፣ የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ 1 ቢሊዮን ብር ደርሷል ብሏል፡፡


ንጋቱ ሙሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page