በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶች የሰሯቸውን ስራዎችና ውጤቶቻቸው ለሌሎች ይፋ ማድረግ እንዳለባቸው ተነገረ።
ይህም ጅርድቶቹ አንዱ ከሌላኛው በመማር እና ተሞክሮ በመውሰድ ይበልጥ ውጤት ያለው ስራ እንዲሰራ ያግዛል ተብሏል።
ይህ የተባለው፣ ራስ አገዝ አሰራር ድርጅቶች ህብረት (Consortium Of Self Help Group Approach Promoters) የአካል ጉዳተኞች ቀንን ምክንያት በማድረግ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ነው።
ራስ አገዝ አሰራር ድርድቶች ህብረት የተለያዩ ድርጅቶች በህብረት ሆነው የመሰረቱት ሲሆን በተለይም በአካል ጉዳተኛ ሴቶችና በህፃናት ላይ የሚደርሱ ችግሮችን እንዲቀንሱ፣ ስለ አካል ጉዳተኝነት ያለው የግንዛቤ ከፍ እንዲል፣ የድጋፍ እና የተሻሉ ፖሊሲዎች እንዲወጡ የሚበረታ ህብረት እንደሆነም ተነግሮለታል።

የህብረቱ ስራ አስኪያጅ ዮሴፍ አካሉ አካል ጉዳተኞች በሁሉም መስክ መካተት እንደሚችሉ ተናግረው በተለይም በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ የሚሰሩ አካላት እርስ በእርሳቸው ቢነጋገሩ ችግሮችን ለማወቅና ለመፍታት እንደሚረዳቸው አስረድተዋል።
በመድረኩም የአዲስ አበባ አካል ጉዳተኞች ማህበር ፕሬዝደንት ወይንሸት ግርማ(ዶ/ር) በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች የተለያዩ ችግሮች እንደሚገጥሟቸው አስታውሰው እነዚህ ችግሮችን ለመቀነስ ከመንግስት ጀምሮ እስከ ግለሰብ ሀላፊነት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።

ከአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ የተወከሉት ወ/ሮ አየሁ ደመቀ አካል ጉዳተኞች ወደ ፊት እንዲመጡ በብርቱ መስራት ይፈልጋል ብለዋል።
በአካል ጉዳተኝነት ዙሪያ ከግንዛቤ በመጀመር ሌሎች የተሻሻሉ አሰራሮች አሉ ያሉት ሀላፊዋ ነገር ግን የሚቀሩ እና መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮችም እንዳሉ ጠቁመዋል።

የአካል ጉዳተኞች ችግር በዓመት አንዴ በሚከበረው የአካል ጉዳተኞች ቀን ብቻ የሚፈታ አይደለም የተባለ ሲሆን በሚወጡ ፖሊሲዎችም ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ተነግሯል።
የአካል ጉዳተኞች ቀን ዘንድሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ32ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው።
ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ያድምጡ….
ማንያዘዋል ጌታሁን
Komentarze