top of page
  • sheger1021fm

ህዳር 28፣ 2015የእስራኤሉ የፍትህ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር ለሊኩድ የፖለቲካ ማህበር መሪው ለቤኒያሚን ኔታንያሁ የመንግስት ማዋቀሪያ ተጨማሪ ጊዜ ሊፈቀድላቸ

ህዳር 28፣ 2015


የእስራኤሉ የፍትህ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር ለሊኩድ የፖለቲካ ማህበር መሪው ለቤኒያሚን ኔታንያሁ የመንግስት ማዋቀሪያ ተጨማሪ ጊዜ ሊፈቀድላቸው አይገባም አሉ፡፡


የፍትህ ሚኒስትሩ ጥያቄውን ለአገሪቱ ፕሬዝዳንት ይሳቅ ሄርሶግ እንዳቀረቡ ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡


ኔታንያሁ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡


አዲስ መንግስት እንዲመሰርቱም እስከ መጪው እሁድ ጊዜ ተሰጥቷቸዋል፡፡


ቤኒያሚን ኔታንያሁ እስካሁን አዲሱን መንግስት የመመስረት ጥረታቸው ዳር አልደረሰላቸውም፡፡


ከተሳካላቸው የኔታንያሁ አዲሱ መንግስት እጅግ ቀኝ ዘመም ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡


የፍትህ ሚኒስትሩም ለኔታንያሁ ተጨማሪ ጊዜ እንዳይፈቀድላቸው የጠየቁት በዚሁ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡


የኔነህ ከበደሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz


Recent Posts

See All

ባለፉት 11 ወራት ምዕራባዊያን ለዩክሬይን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ሲያስታጥቋት ቆይተዋል፡፡ አሁን ደግሞ የአሜሪካ እና የጀርመን ስሪት ታንኮችን ታገኛለች መባሉ ከፍተኛ መነጋገሪያ ወጥቶታል፡፡ የኔነህ ከበደ ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

bottom of page