top of page

ህዳር 27፣2017 - ''የጥራት መንደር'' የተገነባው ለገበያ የሚቀርቡ ምርቶች ጥራትና ደህንነት ለመቆጣጠርና ለማስጠበቅ መሆኑን ተጠቆመ፡፡

  • sheger1021fm
  • Dec 6, 2024
  • 1 min read

ይህንን የሰማነው የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ያዘጋጀው አውደ ርዕይ በከተፈተበት ጊዜ ነው፡፡


ከድርጅቱ የጥራት እውቅና የተሰጣቸው ምርቶች ብቻ የቀረቡበት አውደ ርዕይን የከፈቱት የንግድና ቃጠናዊ ትስስር ሚንስትር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጪ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶች ጥራት እና ደህንነት በተገቢው መንገድ ካልተረጋገጠ ገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ መሆን አይቻልም፡፡


መንግስት ይህን ታሳቢ በማድረግ በ8.2 ቢሊዮን ብር ወጪ የጥራት መንደርን ገንብቷል ብለዋል፡፡


ገበያው አሁን የሚፈልገው ጥራትን ብቻ ሳይሆን ከዛም ያለፈ አሰራርን ተግብሮ ተወዳዳሪ መሆንን ነው የጥራት መንደርም የገነባው ይህንን ታሳቢ በማድረግ ነው ሲሉ ጠቁመዋል፡፡


የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር መዓዛ አበራ ድርጅቱ በሀገር ውስጥም ሆነ ከውጪ የሚመጡ ምርቶች ጥራት ፍተሻ ያደርጋል ሲሉ ነግረውናል፡፡


400 ምርቶች በዚህ ድርጅት ውስጥ የጥራት ፍተሻ ይደረግላቸዋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ አሁንም ተጨማሪ መሳሪያዎች በማስገባት አገልግሎቱን ለማስፋት የ5 ዓመት ትግበራ አቅድ አውጥቶ እየተንቀሳቀስን ነው ሲሉ ያስረዳሉ፡፡


የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት አሁን ባሉት ቴክኖሎጂዎች ከሀገር ውስጥ ተቋማት ባለፈ ለጎረቤት ሃገራት ጭምር አገልግሎት እየሰጠ ነው ያሉን ኢንጅነር መዓዛ አበራ በየጊዜው የሰው ሃይል እና የቴክኖሎጂ ማዘመን ስራው ጎን ለጎን እየተሰራ ይቀጥላል ብለዋል፡፡


በረከት አካሉ



 
 
 

Komentarze


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page