top of page

ህዳር 27፣2017 - በሀገር ቤት ለሚመረቱ የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ምርቶች አስገዳጅ የጥራት ደረጃ እንዲቀመጥ ተጠየቀ።

  • sheger1021fm
  • Dec 6, 2024
  • 1 min read

በሀገር ውስጥ ያለውን የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ ምርቶች ፍላጎት ለማሟላት በተለይ በጨርቅ የሚሰሩ የንፅህና መጠበቂያዎች ጤናን የማይጎዱና ለአጠቃቀምም የተመቹ እንዲሆኑ ለማድረግ የተቀመጠ ደረጃ ቢኖርም አስገዳጅ ባለመሆኑ በዘፈቀደ እንዲመረት በር ከፍቷል ተብሏል።


ይህ የተባለው የፈረንሳይ የልማት ድርጅት በሆነው(AFD) በተሰናዳና የሴቶች የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ አቅርቦት፣ ችግሮቹ ላይና መፍትሄዎቹ ላይ  ትኩረቱን ባደረገ ምክክር ላይ ነው።


ለምክክሩ መነሻ የሆነ ገለፃ ያደረጉት ከኢስት አፍሪካ የህግ አማካሪ ድርጅት የተወከሉት አቶ ሲሳይ ሉጬ የሚመረቱ የንፅህና መጠበቂያዎች በሃገር ውስጥ ያለውን እጥረት ለመሙላት ወሳኝ ቢሆኑም ጤና ላይ እክል እንዳያመጡ ሲመረቱ የግድ አስገዳጅ ደረጃ ሊቀመጥላቸው ይገባል ብለውናል።


የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት በበኩሉ የወር አበባ ንፅህና ምርቶችን በተመለከተ አሁን ያሉ ደረጃዎች አስገዳጅ እንዳልሆኑ  የኢንስቲትዩቱ የጤናና ደህንነት ቁጥጥር ባለሙያ የሆኑት አቶ በፍቃድ ፀጋ ተናግረዋል።


እርሳቸው እንደሚሉት  ምርቶቹ የሚመረቱበት ግብአት በዝርዝር ተለይቶ የግድ ይህንን ማካተት ተብሎ ባለመቀመጡ አስገዳጅ አይደለም፤ ይሁንና ዘርፉን የሚቆጣጠሩ የመንግስት ተቋማት ተመልክተውት በጤናና በአካባቢ ላይ የሚፈጥረው ችግር አለ በሚል ከቀረበ  ደረጃዎቹ ምን ይጎድላቸዋል የሚለው ታይቶ ደረጃቸውን አስገዳጅ ማድረግ ይቻላል ብለውናል።


በሌላ በኩል ለአብዛኛው ተጠቃሚ የሚደርሱት ከውጭ የሚገቡት የንፅህና መጠበቂያዎች የሚጠየቅባቸው የጉምሩክ ቀረጥ እንዲነሳላቸው ተጠይ ቋል፡፡


እንዲሁም በሃገር ውስጥ ሲሸጡ የሚከፈለው ቫት መቅረት እንዳለበት ተነስቷል።


እነዚህና ሌሎችም ተደጋግመው የሚነሱ የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ ምርቶችን እንደ መሰረታዊ ፍጆታ እቃ ተመልክቶ በመጠንም በዋጋም የማህበረሰቡን የመግዛት አቅም ያገናዘበ አቅርቦት መኖር አለበት የሚሉ ጉዳዮች በግልና በመንግስት ተቋማት በተፈጠረው ጥምረት ውይይቶች ተደርገውባቸው  የጤና ሚኒስቴርና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሚመሩት ኮሚቴ መቅረቡን ከኢስት አፍሪካ የህግ አማካሪ ድርጅት ተወክለው የተገኙት አቶ ሲሳይ ነግረውናል።


የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኑት ቁጥጥር ባለስልጣን በበኩሉ መልሶ ጥቅም ላይ የሚውል የንፅህና መጠበቂያ በሃገር ውስጥ ከሚያመርቱ ድርጅቶች አንዳቸውም የመስሪያ ቤቱን የጥራት፣ የደህንነትና ውጤታማነት ማሟላት አለማሟላታቸው እንዳልተረጋገጠላቸው ነግሮናል።


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ያድምጡ ….https://tinyurl.com/yn9z3375


ምንታምር ፀጋው



 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page