top of page

ህዳር 27፣ 2015- ጎሕ ቤቶች ባንክ ስራ በጀመረበት 2014 በጀት ዓመት 8 ወራት ያልተጣራ 7.9 ሚሊየን ብር ማትረፉን ተናገረ

ህዳር 27፣ 2015


ቤት ገዢዎችን፣ ገንቢዎችን፣ አዳሾችን በገንዘብ መደገፉ ዋናው ዓላማው አድርጎ የተቋቋመው ጎሕ ቤቶች ባንክ ስራ በጀመረበት 2014 በጀት ዓመት 8 ወራት ያልተጣራ 7.9 ሚሊየን ብር ማትረፉን ተናገረ፡፡


ከትርፉ ላይ ህጋዊ መጠባበቂያ፣ የረጅም ጊዜ የግብር ዕዳ ወጪ ማስተካከያ እንዲሁም ለብድርና ተሰብሳቢዎች የሚያዝ ተጨማሪ መጠባበቂያ ሲቀነስለት የተጣራ 2.4 ሚሊየን ብር አግኝቻለሁ ብሏል፡፡


ባንኩ በዛሬው ዕለት የመጀመሪያውን ጠቅላላ ጉባኤ አካሂዷል፡፡


በጉባኤው ላይ የባንኩን የ2014 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ያቀረቡት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢው አቶ ጌታሁን ናና ባንኩ ስራ በጀመረ 8 ወራት ውስጥ ያገኘው ውጤት አበረታች ነው ብለዋል፡፡


በዚህም የባንኩ ተቀማጭ 256.6 ሚሊየን ብር፣ በብድር እና ቅድመ ክፍያ የተሰጠ 298.5 ሚሊየን ብር እንዲሁም ጠቅላላ ገቢው ደግሞ 121.7 ሚሊየን ብር መሆኑንን የቦርድ ሰብሳቢው አስረድተዋል፡፡


የጎሕ ቤቶች ባንክ አጠቃላይ ሀብት 1.2 ቢሊየን ብር፣ የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ 780 ሚሊየን ብር መሆኑንን ሰምተናል፡፡


በኢትዮጵያ የቤት ፍላጎቱ ከፍተኛ መሆኑንን የተናገሩት የቦርድ ሰብሰቢው የባንኩ የማደግ እድልና አቅም ከፍተኛ መሆኑንን ተናግረዋል፡፡


ይሁን እንጂ ለቤቶች ብድር የሚውል የረጅም ጊዜ ገንዘብ ማሰባሰብ ለባንኩ ከፍተኛ ችግር ሆኖበታል ብለዋል፡፡


በኢትዮጵያ በተለይ በአዲስ አበባ መሬት ማግኘት ፈታኝ መሆኑን ያነሳው ጎሕ ቤቶች ባንክ ዜጎች የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ይህንን የመሬት አቅርቦት ችግር ለመፍታት ከመንግስት ጋር እየተነጋገርኩ ነው ሲል ሰምተናል፡፡


ጎሕ ቤቶች ባንክ ከሁለት ዓመት በ


ኋላ የተከፈለ ካፒታሉ አሁን ካለበት በእጥፍ ያህል አድጎ 1 ቢሊየን ብር አንዲሆን ወስኗል፡፡


ንጋቱ ሙሉ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page