ጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ፤ 94 ስደተኞችን በአውሮፕላን ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን ተናገረ፡፡
ስደተኞቹ እንዲመለሱ የተደረገው በጀቡቲ ከሚገኘው የዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ጋር በመተባበር ነው ብሏል ኤምባሲው፡፡
ኤምባሲው በህገወጥ መንገድ ድንበር መሻገርን በመተው የሰዎችን ህይወት መቀጠፍ መቀነስ እንደሚያስፈልግም አሳስቧል፡፡
ከኢትዮጵያ ተነስተው በጀቡቲ በማድረግ ወደ ሌሎች ሀገራት ለመሻገር የሚሞክሩ ሰዎች ብዙ እንደሆኑ ይነገራል፡፡
በዚህም የጀልባ የመገለበጥ አደጋ አጋጥሞ ስደተኞች ህይወታቸውን እንደሚያጡ IOM በተደጋጋሚ የሚያወጣቸው መግለጫዎች ያሳያሉ፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments