top of page

ህዳር 26፣2017 - ዘምዘም ባንክ ከሳንቲም ፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽንስ ጋር አብሮ ለመስራት ተስማማ

ዘምዘም ባንክ ከሳንቲም ፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽንስ ጋር አብሮ ለመስራት ተስማማ።


ስምምነቱን የባንኩና የሳንቲምፔይ ሃላፊዎች በዛሬው እለት ተፈራርመውታል፡፡


ስምምነቱ የዘምዘም ባንክ ደንበኞች ለሚፈፅሙት ግብይት እና ለተጠቀሙት አገልግሎት በቀላሉ በሳንቲምፔይ በኩል ክፍያ መፈፀም የሚያስችላቸው ነው ተብሏል።


አገልግሉቱን ለማግኘትም ሳንቲምፔይ በየንግድ ማዕከላት ያከፋፈላቸውን ኪውአር ኮድ በተቀሳቃሽ የእጅ ስልካ ስካን በማድረግ በቀላሉ ክፍያ መፈፀም የሚያስችል መሆኑ ተነግሯል።

ይህም በጤና ተቋማት፣ በአልባሳት ደብሮች፣ በስጦታ ዕቃ መደብሮች፣ ግባታ ዕቃ መሸጫዎች፣ የኤሌክትኒክስ መሸጫዎች፣ በስቴሽነሪዎች፣ በመኪና ዕቃ እና ጌጣ ጌጥ መሸጫዎች፣ ሆቴሎች እና በካፌዎች እና ሌሎችም በርካታ አገልግሎት ቦታዎች ደንበኞችን ለተጠቀሙት አገልግሎት እንዲሁም ለፈጸሙት ግዢ በተንቀሳቃሽ የእጅ ስልካቸው ብቻ ክፍያ መፈጸም እንደሚችሉ በስምምነት ስነስርዓቱ ላይ ተነግሯል።


አገልግሎቱ ክፍያን ከማቅለል በተጨማሪ ደንበኞች ካሉበት ሆነው የተለያዩ ክፍያዎችን መፈጸም ያስችላቸዋልም ሲብል ሰምተናል።


ዘምዘም ባንክ በሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ ባንክ አገልግሎት የሚሰጥ ባንክ ነው፡፡


ሳንቲምፔይ ክፍያዎችን ለመፈጸም እና ሌሎች አስፈላጊ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ለማቅረብ የሚያስችል የክፍያ መፈጸሚያ መድረክ ነው።


አሁን ላይ በክፍያ መፈጸሚያ መድረኩ ቢያንስ አንድ ጊዜ የገንዘብ ዝውውር ያደረጉ ከ8 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች አሉኝ ብሏል፡፡



תגובות


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page