ህዳር 26፣2017 - አዲስ የመሰረታዊ መድኃኒት መዘርዝር መሰናዳቱ ተነገረ
- sheger1021fm
- Dec 5, 2024
- 1 min read
በኢትዮጵያ አሁን ካለው የጤና ሥርአዓትና የበሽታ መከላከል ስራዎች ጋር የተጣጣመነ የመድኃኒት አቅርቦት እንዲኖር አዲስ የመሰረታዊ መድኃኒት መዘርዝር መሰናዳቱ ተነገረ።
በኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣንና ሌሎች በጋራ የሚሰሩ ተቋማት ጋር በመሆን የተሰናዳው የተሻሻለው የመሰረታዊ መድሀኒት መዘርዝር 77 አይነት አዳዲስ መድኃኒቶች እንደተካተቱበት ተነግሯል።
መሰረታዊ የመድኃኒት መዘርዝሮች ማለት በጤና ተቋማትና የመድኃኒት መሸጫ መደብሮች መገኘት ያለባቸው እና የተለያዩ ጥናቶችና የበሽታ ቅኝቶች ተደርጎ እንደሚሰናዱ የነገሩን በኢትዮጵያ #ምግብና_መድኃኒት_ባለስልጣን የመድኃኒት መረጃና አግባባዊ አጠቃቀም ዴስክ ሀላፊው አቶ ኃይለማርያም እሸቴ ናቸው።
ከዚህ ቀደም የነበረውን የመድኃኒት አጠቃቀም መዘርዝር በተመለከተ የተለያዩ ሀገር አቀፍ የዳሰሳ ጥናቶች መከናቸውን የሚናገሩት አቶ ኃይለማርያም ከ #ጤና_ሚኒስቴር እንዲሁም ሌሎች የጤና ስርዓቱ ላይ ካሉ ተቋማትም የተሳተፉበት እንደነበር ተናግረዋል።
የተሻሻለዉ የመሰረታዊ መድሃኒት መዘርዝር የአገሪቱን ብሔራዊ የኤች አይቪ ቲቢ እና ሌሎችም ህክምና አሰጣጥ መመሪያዎች ጋር የተስማማ እንዲሆን ተደርጎ የተሰናዳ ነው ተብሏል።
መመሪያው የጤና ሚኒስቴርን ጨምሮ የሁሉም ክልል የመድኃኒት ተቆጣጣሪዎች በተገኙበት በመጪዎቹ ቀናት ይፋ እንደሚደረግ ከኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ሰምተናል።
ምህረት ስዩም
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Kommentare