ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ ህጋዊ መሆኑን ያረጋገጠው የአባይ ውሃ የትብብር ማዕቀፍ (CFA) ለአንዳንድ ሀገራት አዲስ ፍላጎትን የጫረ ይመስላል ተባለ፡፡
የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫቸው ህጋዊነቱን ያረጋገጠውን የኮፕሬቲቭ ፍሬም ወርክ አግሪመንት ወይም #CFA በትብብር መቀበሉ ለሁሉም ሀገራት ይበጃል ያልፈረሙ ሀገራትም ቢቀላቀሉ ይሻላል ይህ ሳይሆን ግን በጉዳዩ ዙሪያ አዳዲስ ህጋዊ ያልሆኑ መንገዶችን መከትል ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡
ከሶማሊያ ሪፖብሊክ በኩል የማያባራ ትንኮሳ እና ዛቻ ወደ ኢትዮጵያ እየተሰማ ነውና በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ግን ምላሽ ሲሰጥ አይሰማም የተባሉት አምባሳደር ነቢያት ‘’ሀላፊነት የሚሰማን ስለሆነ ነገሮችን ማባባስ አንፈልግም’’ ብለዋል፡፡
የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በወቅታዊ ጉዳዮች መግለጫቸው በዜጋ ተኮር፣ ዲፕሎማሲ እና በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ዙሪያ ልዩ ልዩ ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል፡፡
የኔነህ ሲሳይ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments