የስራገበያው በኢንዱስትሪዎች ፍላጎት ሊመራ ቢገባውም በኢትዮጵያ ግን በተገላቢጦሽ አቅርቦቱ ፍላጎቱን ይመራል ሲባል ሰምተናል፡፡
በኢትዮጵያየስራ ገበያ በስፋት የሚታየውን የክህሎት ክፍተት ለመሙላት ምን ቢደረግ ይበጃል በሚል ዛሬ በራዲሰን ብሉ ሆቴል በተሰናዳ ዝግጅት ላይ ነው እነዚህ ሀሳቦች ሲነሱ የሰማነው።
ስራንለመከወን ከሚፈለገው የሞያና የቴክኒክ እውቀት ጎን ለጎን አንድ ሰው ሊላበስ የሚገባው፤ የባህሪ እና የክህሎት ብቃት (ሶፍትስኪል) የኢትዮጵያ ስራ ገበያ ትልቁ ርሃብ ነው ተብሏል፡፡
ከ 1 ዓመትበፊት የተመሰረተው የክህሎት ልማት ማህበር (Association for talent development) ባሰናዳው በዚህዝግጅት ላይ የስራው ቀዳሚ ባለቤት የሆነው የስራና ክህሎት ሚኒስቴርን ጨምሮ ሌሎች ይመለከታቸዋል የተባሉ ተቋማት ተሰባስበው የክህሎት ስልጠና የሚለካና የሚቆጣጠር ለማድረግ ምን እንስራ፤ አገር አቀፍ ስርዓትስ እንዴት ይኑረንብለው መክረዋል፡፡
የስራእና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ንጉሱጥላሁን ሲናገሩ እንደሰማነው በስራ ገበያው ውስጥ ከፍተኛ የሰራተኛ ፍላጎት በኢንዱስትሪዎች በኩል ቢኖርም በሌላ ጎን ደግሞ ሀገሩ በከፍተኛ ስራ ፈላጊና ሥራ አጦች ቁጥር ተሞልቷል ብለዋል፡፡

የዚህክፍተት መነሻ ከመደበኛው እውቀት ባለፈ መደበኛውን የቴክኒክ እውቀት በወጉ ለማላወስ የሚረዳ የክህሎት ወይም ሶፍት ስኪል እውቀት በገበያው በሚፈለገው ልክ አለመገኘቱ ነው ብለዋል፡፡
የስራእና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢንዱስትሪዎች ጋር በሚያደርገው ምክክር ይህ ሀሳብ ተደጋግሞ ይነሳል ያሉት አቶ ንጉሱ እንደምሳሌም ከ65,000 በላይ ሰራተኞችን የያዘው ሜድሮክና ሌሎች መሰል ግዙፍ ተቋማት እውቀትን ከክህሎት ያስማማ ሰራተኛን በማጣት እየተቸገሩ ነው ብለዋል፡፡
ይህንንችግር ለመፍታት ከዓመት በፊት የተቋቋመው አሶሴሽን ኦፍ ታለንት ዴቨሎፕመንት (ATDE) የቦርድ ሰብሳቢዶ/ር ገመቹ ዋቅቶላ ለተበታተነው የክህሎት ስልጠና ስራ ሥርዓት ለማበጀት ማህበሩ መመስረቱን አስረድተዋል፡፡
በአለምአቀፍ ደረጃ በቅርብ ጊዜ በተጠና ጥናት የክህሎት ክፍተቱ በገንዘብ ሲሰላ መጠኑ ወደ 8.5 ቢሊዮን ዶላር ነው ብለዋል፡፡
ይህችግር በሁሉም ሀገራት በጊዜ መፍትሄ ካልተፈለገለት በአውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር 2030 በዓለም ዙሪያ ወደ 85 ሚሊየን የስራ እድል በዚሁ የክህሎት ክፍተት ምክንያት ተቀጣሪ ሊያጣ እንደሚችል ጥናት አረጋግጧል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያምበተለይም ባንኮችና ኢንሹራንሶች ለክህሎት ስልጠና የሚያወጡት ወጪ ወደ 1.5 ቢሊየን ብር ገደማ እንደሆነ ያነሱት ዶ/ር ገመቹ ስልጠናው ግን የሚለካና በወጉ የሚመዘን ባለመሆኑ ውጤቱን ወጥ በሆነ መንገድ ማወቅ አይቻልም ብለዋል፡፡
በተለይየስራ ላይ ስልጠናን ማሳደግና የስራ ቦታን እንደ ስልጠና ማዕከልም አድርጎ መውሰድ ውጤታማ ሰራተኞችን ለማግኘት፣ ተለዋዋጭ የሆነውን ዓለምም ተለማምዶ ለመስራት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
ዛሬየተካሄደውን ምክክር ተከትሎም በሀገር አቀፍ ደረጃ የክህሎት ስልጠና የእራሱ የሚመራበት መለኪያና መቆጣጠሪያ ኖሮት በፖሊሲ የተደገፈ እንዲሆን ማስቻል የማህበራቸው ፍላጎት እንደሆነም ዶ/ር ገመቹ ተናግረዋል፡፡
የስራእና ክህሎት ሚኒስቴርም የክህሎት ስልጠና ደረጃ ወጥቶለት፣ መለኪያም ተዘጋጅቶለት እውቅና ማግኘት በሚችልበት ደረጃ መመራት እንዲችል ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከማህበሩ ጋር ተቀራርቦ እንደሚሰራ ተነግሯል፡፡
ቴዎድሮስ ወርቁ
የሸገርንወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments