top of page

ህዳር 25፣20171.5 - ሚሊዮን ብር ጉቦ ጠይቋል የተባለ ተጠርጣሪ የመንግስት ሰራተኛ፤ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነገረ

  • sheger1021fm
  • Dec 4, 2024
  • 1 min read

1.5 ሚሊዮን ብር ጉቦ ጠይቋል የተባለ ተጠርጣሪ የመንግስት ሰራተኛ፤ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነገረ።


ጉቦ ጠይቋል የተባለው የመንግስት ሰራተኛ፤ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቅንጫፍ ጽህፈት ቤት የይዞታ ማስተካከል ቡድን መሪ መሆኑ ተነግሯል።


አሸብር አበባው ታደሰ የተባለ ተጠርጣሪው ሆን ብሎ መረጃ በማጉደል፣ በሥልጣን ያለአግባብ በመገልገል እና #ጉቦ በመቀበል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ነው የተናገረው።


የወ/ሮ ሙሉ ካህሺን ሕጋዊ ወኪል የሆኑት አቶ ደራራ ዲንሳ ኢረና በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የሚገኝ የቦታ ይዞታቸው በመሬት ይዞታ ምዝገባ ኤጀንሲ እንዲረጋገጥላቸው ለአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቅንጫፍ ጽህፈት ቤት አመልክተው፤ ተጠርጣሪው የማይገባ ጥቅም በመፈለግ ከአመልካች ማኅደር ላይ #መረጃ በማጉደል እና ጉዳያቸውን በማጓተት ሲያጉላላቸው ከቆየ በኋላ መረጃውን አሟልቶ ወደ ሚመለከተው አካል ለመላክ አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር ጉቦ መጠየቁን የምርመራ ቡድን ደርሶበታል ተብሏል፡፡

ባለጉዳዩ አቶ ደራራ ዲንሳ የተጠየቁትን #ገንዘብ ወደ ተጠርጣሪው የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ያስገቡ መሆናቸውን ሕዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ለምርመራ ቡድኑ ጥቆማ አቅርበው ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር ሊውል እንደቻለ ፖሊስ አስረድቷል፡፡


የምርመራ ቡድኑ የተጠርጣሪውን የእምነት ክህደት ቃል በመቀበል፣ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ የ10 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ  የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የተጠየቀውን የጊዜ ቀጠሮ እስከ ሕዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም  ድረስ መፍቀዱ ፖሊስ ተናግሯል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page