top of page

ህዳር 25፣2017 - የአፋር እና የሶማሌ ክልሎች የአስረኛ ልውውጥ ማድረጋቸው ተሰማ

በአፋር እና በሶማሌ ክልል መካከል ለበርካታ ዓመታት በተደጋጋሚ ሲደረጉ የነበሩ ጦርነቶች እና ግጭቶች በሰላም ስምምነት መፈታቱን ተከትሎ ከሁለቱም ክልሎች በኩል በጦርነት እና በግጭት ዙርያ ተይዘው የነበሩ የእስረኞች ልውውጥ ዛሬ ተከናዉኗል፡፡


ሁለቱ ክልሎች አስረኞችን የተለዋወጡት በአፋር ክልል በአዋሽ ከተማ መሆኑ ተነግሯል።


የእስረኞቹ ልውውጥ የተደረገው የፌደራል ተወካዮች፣ የፌደራል የፀጥታ አካላት እና የሁለቱም ክልሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው ሲል የተናገረው የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ነው።


ፅህፈት ቤቱ ምን ያህል እስረኞችን እንደተለዋወጡ አላብራራም፡፡


የአፋር ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ ጋዶ ሃሞሎ በሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች መካከል የነበሩ ግጭቶች እና ጦርነቶች በሰላም እንዲፈታ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካል ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች መሃል ሰላም እንዲሰፍን እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር ሁሉም አካል ቅድሚያ ለሰላም ሰጥቶ መስራት እንዳለበት እና ልዩነቶችን በንግግር እና በውይይት መፍታት እንደሚያስፍልግም ጠቁመዋል።


የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል አብዲ አሊ ዚያድ በበኩላቸው የተገኘውን ሰላም በማጠናከር የሁለቱም ህዝቦች አንድነትን እና ውንድማማችነትን እንደሚያስቀጥሉ ተናግረዋል።

ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page