top of page

ህዳር 25፣2017 - ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ ግጭቶች መቶ በመቶ መቆም የለባቸውም ሲል የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ

ኮሚሽኑ ይህን የተናገረው በዛሬው እለት ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አጀንዳዎቹን በተቀበለበት ወቅት ነው፡፡


የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዕያ የተጀመረውን ምክክር ለማካሄድ ግጭት 100 በመቶ መቆም የለበትም ሲሉ ተናግረዋል፡፡


ይህን ምክክር ለማካሄድ ግጭት 100 ፐርስንት መቆም የግድ የለበትም ምክኒያቱም ምክክር በግጭት ጊዜ ይካሄዳል ፣ምክክር ግጭት ካለቀ በኋላ ይካሄዳል እንዲሁም ምክክር ጦርነት ወይንም ግጭት እንዳይመጣም ይካሄዳል ሲሉ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዕያ ተናግረዋል፡፡

ከመጀመሪያው ጀምሮ ኮሚሽኑ ሲጠይቅ የነበረው በሁሉም የአገራችን ክልሎች አንጻራዊ ሰላም እንዲመጣ አስቻይ ሁኔታዎች ከፌደራል መንግስትም ከክልል መንግስትም በአጠቃላይ ከህዝቦቻችንም በኩል ጫና ተደርጎ ወደ አንጻራዊ ሰላም እንድንመጣ፣ ወደ ትጥጥቅ የወሰዱን ጥያቄዎች በሙሉ በአጀንዳ መልክ ወደ ኮሚሽኑ እንዲመጡ የሚስችል ሁኔታ እንዲፈጠር ጥያቄ ነበር ሲሉ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡


በቡዙ ቦታ የተሻለ ሁኔታ እያየን ነው ያሉት ዋና ኮሚሽነሩ ለምሳሌም በምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ላይ ያለውን ሁኔታ ታውቃላቸሁ ነገር ግን ስራችንን ሙሉ በሙሉ ሰርተን ወጥተናል ብለዋል፡፡


በምዕራብ ኦሮሚያ ስላለው ሁኔታም በየጊዜው የሰላም ሂደቶች እንዲመጡ የፌደራል መንግስትን የክልል መንግስትን ህዝቦቻችንን እና በትጥቅ ትግል ላይ ላሉት ጥያቄዎችን እናቀርባለን ሲሉ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዕያ ተናግረዋል፡፡


ያሬድ እንሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page