የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ በሚኒስትሮቸ ምክር ቤት ከፀደቀ ስምንት ወራት ሞላው፡፡
በኢትዮጵያ ባለፉት 30 ዓመታት ለተፈፀሙ እና አሁን እየተፈፀሙ ላሉ የጦርነት፣ የግድያ፣ የማፈናቀል እና ሌሎች በደሎች አጥፊዎችን በህግ ፊት ለማቆም፣ ተጎጂዎችንም ለመካስ የሽግግር ፍትህ መፍትሄ ተደርጎ ቀርቧል፡፡
ይህ #የሽግግር_ፍትህ_ፖሊሲ ወጥቶለት ከፀደቀ ስምንት ወራት የሞላው ሲሆን እንደ እቅዱና እንደታሰበው ቢሆን ኖሮ በዚህ ወቅት የፖሊሲው ማስተግበሪያ ስልቶች ለመተግበር የሚያስችሉ የተቋማት ማቋቋሚያ አዋጆች መፅደቅ ነበረባቸው፡፡
የሽግግር ፍትህ ልዩ አቃቢ ህግ፣ ልዩ ችሎት፣ የእውቀት ምህርት እና #ማካካሻ ኮሚሽን እንዲሁም የሁሉም ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጆች ላይ የህዝብ ውይይት ባለፈው ጥቅምት ወር እንዲያልቅ በዚህ በህዳር ወር ደግሞ አዋጆቹ በህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት እንዲፀድቁ ታስቦ ነበር፡፡
ታዲያ ስራው ከምን ደረሰ፣ የማቋቋሚያ አዋጆች ላይ የህዝብ ውይይት ተደረገ ወይ? እንዲፀድቅስ ለፓርላማ ቀረበ ወይ? ስንል በፍትህ ሚኒስቴር የሽግግር ፍትህ የተቋማት ቅንጅታዊ አመራር ሴክሬተሪያት ሀላፊ አቶ አወል ሱልጣንን ጠይቀናቸዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments