top of page

ህዳር 24፣2017 -የገንቢዎች የሊዝ ፈቃድ የሚሰረዝበት የህግ ማዕቀፍ ማሻሻያ ያስፈልገዋል ተባለ

  • sheger1021fm
  • Dec 3, 2024
  • 1 min read

የገንቢዎች የሊዝ ፈቃድ የሚሰረዝበት የህግ ማዕቀፍ ማሻሻያ ያስፈልገዋል ተባለ፡፡


ተሻሽሎ ለፓርላማው በቀረበው የከተማ መሬትን በ #ሊዝ ለመያዝ የተሰናዳው ረቂቅ አዋጅ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች የከተማ መሬትን በድርድር መስጠትን የሚፈቅደው ድንጋጌ ለ #ሙስና ያጋልጣል የሚል ስጋት ቀርቦበታል፡፡


በረቂቅ አዋጁ ላይ ጉዳዩ ያገባናል ያሉ ባለሞያዎች እና ተቋማት ይስተካከል ያሉት ነጥብም በፓርላማ ተገኝው አስተያየት ሰጥተውበታል፡፡


ረቂቅ ህጉ ከተሞች በየዓመቱ ከሚያቀርቡት #መሬት 20 በመቶው ለመኖሪያ ቤት መገንበያ እንዲሆን የሚያስገድድ ነው፡፡


በተጨማሪም የቀድሞው የሊዝ ህግ ከፀደቀበት ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳይሰጥ የተያዘ ሙሉ በሙሉ ወደ መሬት ባንክ እንዲመለስ ያስገድዳል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…



ትዕግስት ዘሪሁን

Comentários


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page