top of page

ህዳር 24፣2017 የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ 10ሩ ወደ ‘’ልዩ የኢኮኖሚ ዞን’’ ማደጋቸው ተነገረ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ 10ሩ ወደ ‘’ልዩ የኢኮኖሚ ዞን’’ ማደጋቸው ተነገረ፡፡


ኮርፖሬሽኑ ከሚያስተዳድራቸው 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና መካከል 10ሩ ወደ ‘’ልዩ የኢኮኖሚ ዞን’’ ማደጋቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከላከው ደብዳቤ ላይ ተመልክተናል።


ወደ ‘’ልዩ ኢኮኖሚ ዞን’’ ያደጉት የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ተገምግመውና አስፍላጊውን መስፈርት አሟልተው በመገኘታቸው ነው ተብሏል፡፡

ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ወደ ‘’ልዩ ኢኮኖሚ ዞን’’ ማደጋቸው የግል ዘርፉ በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በአገልግሎት እና ሌሎች ልማታዊ ኢንቨስትመንቶች ላይ እንዲሳተፉ ለማበረታታት፣ የሀገሪቱን የውጪ ባለሀብት ቀጥታ ኢንቨስትመንት የመሳብ እንቅስቃሴ ለማጠናከር፣ በዓለም ዓቀፍ የንግድ ሰንሰለት ለማስፋፋት ይረዳል ሲል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ተናግሯል፡፡


ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ያደጉት ኢንዱስትሪ ፓርኮች የአዳማ፣ የባህርዳር ፣ የቦሌ ለሚ፣ የደብረ ብረሃን፣ ሀዋሳ ፣ የጅማ፣ የቂሊንጦ ፣ የኮምቦልቻ፣ የመቀሌ እና የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንደሆኑ ተጠቅሷል፡፡


ማንያዘዋል ጌታሁን

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page