ህዳር 23፣2017 - እየተፈጠረ ያለው የስራ እድል ከህዝቡ ቁጥር እድገት ጋር የሚጣጣም እንደልሆነ ተነግሯል
- sheger1021fm
- Dec 2, 2024
- 1 min read
የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው።
ይሁንና በሀገሪቱ እየተፈጠረ ያለው የስራ እድል ከህዝቡ ቁጥር እድገት ጋር የሚጣጣም እንደልሆነ ተነግሯል፡፡
በኢትዮጵያ የስራ አጥ ቁጥሩ ከፍተኛ ነው፡፡
ከሀገሪቱ ህዝብ ብዛት አብዛኛውን ቁጥር የሚይዘው ደግሞ በስራ እድሜ ላይ ያሉ ናቸው፡፡
ቆስጠንጢኒዮስ በረሃተስፋ (ዶ/ር) የምጣቤ ሃብት በለሞያ ናቸው፡፡
እሳቸው በሀገሪቱ ያለውን ወጣት ወደ ስራ ማስገባት ካልተቻለ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚዊ ቀወስ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካም ቀወስም ማስከተሉ አይቀርም ይላሉ፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ያሬድ እንዳሻው
Comments