top of page

ህዳር 21፣2017 - ‘’የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎችን ጥገና ወጣቶች ስልጠናዎችን እንዲያገኙ እያመቻቸሁ ነው’’ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት

‘’የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎችን ጥገና አስመልክቶ ወጣቶች ከወዲሁ በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገራት ስልጠናዎችን እንዲያገኙ እያመቻቸሁ ነው’’ ሲል የፌደራል ቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ተናግሯል፡፡


መንግስት የኢትዮጵያ የትራንስፖርት ዘርፍ ወደ #ታዳሽ_ሀይል በማዞር የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች በስፋት ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ እያደረገ ነው፡፡


እነዚህ ተሸከርካሪዎች ለሀገሪቱ አዲስ እንደመሆናቸው ለሚያጋጥሟቸው ብልሽቶች የሚያስፈልጉ የጥገና ባለሙያዎችን ለማፍራት በሀገር ውስጥ በዘርፉ ልምድ ባላቸው ሀገራት የትምህርት እድል እየተመቻቸ መሆኑን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ነግረውናል፡፡

በዚሁ የስልጠና ጉዳይ በተለይም በቻይና ከሚገኙ #የኤሌክትሪክ_ተሸከርካሪ አምራች ድርጅቶች እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር ስምምነቶች መፈረማቸውንም ስምተናል፡፡


በዚህም መሰረት በመጀመርያ ዙር ወደ ቻይና ተጉዘው ስልጠናዎችን ወስደው የተመለሱ ወጣቶች ወደ ስራ የገቡ ሲሆን መሰረታቸውን በቻይና ያደረጉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም በኢትዮጵያ ውስጥ ስልጠና መስጠት ጀምረዋል ብለውናል፡፡


ከዚህ በተጨማሪም እየተስፋፋ በመጣው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ላይ እንዲሁም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ላይ በልዩነት የሚሰራ ራሱን የቻለ የቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም በሀገር ውስጥ ለመክፈት እንቅስቃሴ ተጀምሯል ተብሏል፡፡


በመጪዎቹ 10 ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ ተሸከርካሪዎች 95 በመቶ የሚሆኑት የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ እደንዲሆኑ ለማድረግ መታቀዱን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚንስቴር ተናግሯል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page