ካለፈው ዓመት ጥር ወር ወዲህ ከ20,000 በላይ ኤርትራዊያን ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ ይገመታል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛው የሥደተኞች ኮሚሽን (UNHCR) ተናገረ፡፡
ኤርትራዊያን፤ በሰሜን አፋር እና ትግራይ ክልል በኩል አለም አቀፍ ጥበቃ እና መሰረታዊ እርዳታ ለማግኘት ወደ ኢትዮጵያ እየጎረፉ ነው ብሏል፡፡
ካለፈው ዓመት ጥር ወር ወዲህ ከ20,000 በላይ #ኤርትራዊያን ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ ይገመታል ሲል ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርት ጠቅሷል።
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ከ180,000 በላይ ኤርትራዊያን #ስደተኞች ተመዝግበው ይገኛሉ ብሏል።
ለእነዚህ ጥገኝነት ፈለጊዎች አና እርዳት ጠያቂዎች ገና ከመመጣታው ጀምሮ መደገፍ ወሳኝ ነው ሲልም ድርጅቱ አሳስቧል።
ለዚህም ሲባል ምዝገባ ማድረግ እና መሰነድ ወሳኝ ናቸው ተብሏል።
#UNHCR ወደ ኢትዮጵያ ለገቡ ኤርትራዊያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ምዝገባ አንዲካሄድ መንግስትን ለመደገፍ ዝግጁ መሁኑንም አስረድቷል።
ምዝገባው መሰረታዊ አገልግሎቶች የሆኑትን እንደ ጤና፣ ትምህርት እና ከቤተሰብ ጋር መልሶ ለመቀላቀል ያግዛል ብሏል።
በጠቃላይ ኢትዮጵያን አስጠልይን ብለው የመጡ እና የተመዘገቡ ስደተኞች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን 71 ሺህ በላይ ደርሷል፡፡
ከእነዚህ ውስጥ 80 በመቶዎቹ ሴቶችና #ህጻናት መሆናቸው ተነግሯል፡፡
በሱዳን ያለውን የእርስ በርስ ጦረነት ሽሽት ኢትዮጵያ የመጡ ስደተኞች ብቻ 64 ሺህ 669 መድረሱን ኮሚሽኑ በሪፖቱ አስረድቷል፡፡
በሀገሪቱ ተጠልለው ለሚገኙ ስደተኞች ምግብ ጨምሮ የተለያዩ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት ላለንበት የፈረንጆቹ ዓመት 426 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተጠቅሷል፡፡
ይሁን እንጂ እስካሁን ከለጋሾች የተገኘው ግመሹን አንኳን ያሆነ(43 በመቶ) ብቻ ነው ተብሏል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments