የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ላይ ያደረግሁት ለውጥ ባለፉት ሶስት ወራት የባንኮች የውጭ ምንዛሪ ክምችት እንዲጨምር አድርጓል ይላል፡፡
ሸገር ራዲዮ ስለጉዳዩ የጠየቀው የግል ባንክ በበኩሉ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ቢጨምርልንም ነጋዴዎች ኤልሲ ከከፈቱ በኋላ ክፍያውን የሚፈፅሙት ከወራት በኋላ ስለሚሆን እና የውጭ ምንዛሪ ተመኑም ተለዋዋጭ ስለሆነ ወደ ቁጥር ገበያው እንዲያማትሩ አድርጓል ብሏል፡፡
ለዚህም መንግስት የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል፡፡
ምንታምር ፀጋው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments