አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት አካል የሆነውን የትምህርት ቤት ክፍያ መፈፀሚያ አገልግሎት (E School Fee) ዛሬ ስራ አስጀምሯል፡፡
#የአዲስ_ኢንተርናሽናል_ባንክ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ከተለመዱት ከግብይትና ከገንዘብ ማስተላለፍ ባለፈ በርካታ አገልግሎቶችን ይሰጣል ተብሏል፡፡
የቼክ ይዘጋጅልኝ ጥያቄ ለማቅረብ፣ የቼክ ክፍያን ለማገድ፣ የኢቲኤም ካርድን አገልግሎት እንዳይሰጥ ለማድረግና ኪው አር ኮድን በመጠቀም ግብይት ለመፈፀም በባንኩ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ማግኘት እንደሚቻል ሰምተናል፡፡
ባንኩ በአዲስ አበባ ኢንተርሌግዠሪ ሆቴል ዛሬ የዲጂታል የት/ቤት ክፍያ አገልግሎትን ሲያስጀምር እንደሰማነው ባንኩ #የሞባይል_ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ቁጥር ወደ 93,000 ተቃርቧል ብሏል፡፡
የአዲስ ኢንተርናሽናል ሞባይል ባንኪንግ በመጠቀም ዛሬ ስራ በጀመረው በአዲስ ዲጂታል የትምህርት ቤት መክፈያ ሥርዓት ወላጆችና አሳዳጊዎች ከማስመዝገብ ጀምሮ የተለያዩ ክፍያዎችን ባሉበት ሆነው ለት/ቤት መክፈል ይችላሉ ተብሏል፡፡
በተጨማሪም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ያለ #መታወቂያ በጣት አሻራ ብቻ የሚገለገሉበት የቁጠባ አገልግሎትም እሰጣለሁ ብሏል፡፡
የባንኩ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ወንድወሰን አሰፋ፤ ባንኩ ለደንበኞች የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ይበልጥ ለማዘመን ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል ጊዜ ቆጣቢና ለደንበኞች አመቺ ዲጂታል አማራጮችን ማቅረብ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
Comments