ህዳር 21፣2017 - በስልጣን ሽኩቻ፣ ለአንድ ከተማ ሁለት ከንቲባ እስከመሾም የተደረሰበት የትግራይ ክልል ጉዳይ
- sheger1021fm
- Nov 30, 2024
- 1 min read
ለሁለት ዓመታት በጦርነት የደቀቀው የትግራይ ክልል ከሰላም ስምምነቱ በኋላ በመልሶ ግንባታ ያንሰራራል የሚል ግምት ነበር፡፡
ይሁንና በህወሃት ባለስልጣናት መካከል የተፈጠረው መከፋፈል የማንሰራራት ተስፋው ተስፋ ብቻ ሆኖ እንዲቀር አድርጎታል እየተባለ ነው፡፡
ከስልጣን ሽኩቻ ባለፈ የትግራይ የፀጥታ ሀይል እርምጃ እንዲወስድ አንዱ በሌላው የህወሃት ቡድን ላይ የማነሳሳት ተግባር እየፈፀሙ በመሆኑ ነገሩ ወደ ግጭት እንዳያመራም ስጋት ፈጥሯል፡፡
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስለ ስጋትና መፍትሄው ምን ይላሉ?
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Commentaires