‘’ድሽታ ግና’’ በሚል የሚጠራው የአሪ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል ዛሬ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ እየተከበረ ነው፡፡
በዓሉ ዘንድሮ እየተከበረ ያለው ለዘጠነኛ ጊዜ ሲሆን መሪ ቃሉም ‘’ባህል፤ ለሠላም፣ ለአብሮነትና ለልማት’’ በሚል ተሰይሟል፡፡
የድሽታ ግና በዓል፤ የምስገና፣ የፍቅር፣ የመረዳዳት፣ የዕርቀ ሰላም፣ እና መሰል እሴቶች የሚገለጹበት እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ጥላቻን አርቀው፣ ሰላምን የሚያሰፍኑ ባህላዊ እሴቶች ተጠብቀው እንዲቆዩ ያለው ድርሻም የሚናቅ አይደለም ሲባልም ሰምተናል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞንና በሌሎች አካባቢዎች በተለየ መልኩ የሚከበረው የድሽታ ግና በዓል በቀደሙት ዓመታት ትኩርት ተነፍጎት ቆይቷል ተብሏል፡፡
ዛሬ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ በዓሉ ሲከበር፣ ብሄረሰቡን የሚገልፁ ባህላዊ ጭፈራዎችና ሙዚቃዎች ቀርበዋል።
በመድረኩ ለአቅመ ደካሞች ዘይትና ዱቄት የተበረከተላቸው ሲሆን በአሪ ዞን ብቻ የሚገኙ ምርቶችና ቅመማ ቅመሞችም ተጎብኝተዋል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ሂሩት ካሳው(ዶ/ር) እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በመድረኩ ተገኝተዋል።
ገዛ ጌታሁን
Comments